በአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል አስተባባሪነት የተካሄደው የደም ልገሳ መርሃ ግብር በታላቅ ስኬት ተከናወነ
ሁዳ መልቲ ሚዲያ | ነሐሴ 11 2018 ዓ.ል (ረቢዑል አወል 04፣ 1448 ዓ.ሂ)
የአዲስ አበባ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ደምና ህብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ታላቅ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በታላቅ ስኬት ተካሂዷል።
ይህ መርሃ ግብር የወጣቶች ካውንስሉ የ2018 ዓ.ል የክረምት የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ አካል የሆነና የዜጎችን ህይወት ለመታደግ ያለመ የበጎ አድራጎት ተግባር ነው።
በዚህ የተቀደሰ መርሃ ግብር ላይ የሃይማኖት አባቶችና ከፍተኛ አመራሮች በአካል ተገኝተው ደማቸውን በመለገስ አርአያነታቸውን አሳይተዋል፡
ሼህ ሃጂ ሱልጣን አማን ኤባ – የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚደንት
ሼህ ሙሐመድ ሸሪፍ – የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት
ኡስታዝ ሺሐቡዲን ሼህ ኑራን – የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የአስተዳደራዊ ጉዳዮችና ተቋማዊ ልህቀት ምክትል ፕሬዝዳንት
በተጨማሪም ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የካውንስሉ አባላት፣ የከተማዋ ሙስሊም ወጣቶችና ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በመርሃ ግብሩ ላይ በነቃ ሁኔታ በመሳተፍ ደማቸውን ለገሰዋል።
"ደም መለገስ የሰውን ህይወት ከመታደግ ባሻገር የወጣቶች ለሀገራቸውና ለማህበረሰባቸው ያላቸውን ቁርጠኝነት፣ አጋርነትና ወንድማማችነት የሚያጎላ ታላቅ ሰብአዊ እሴት ነው!"
#ሁዳ_መልቲ_ሚዲያ #HudaMultimedia
ሀያት ሁሴን
2
1August 17, 2026 2K









