ከሀራም_ለመላቀቅ_ይፈልጋሉን ? 🤔 هل تريد الإقلاع من الذنوب 🤲 ከሀራም (ከአላህ… — ☀ሁዳ መልቲሚዲያ |HUDA MULTIMEDIA — TG.ME

#ከሀራም_ለመላቀቅ_ይፈልጋሉን ? 🤔
هل تريد الإقلاع من الذنوب 🤲

ከሀራም (ከአላህ ክልከላዎች) መራቅና ወደ ሐላል ማዘንበል የጠንካራ እምነት (ኢማን) ምልክት ነው ። በዚህ መልካም መንገድ ላይ ለመጽናትና መንፈስዎን ለማጠናከር የሚረዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ 📝

1️⃣ ሶላትን በወቅቱ በጀመዓ መስገድ፦ ሶላት ከእኩይና ከሀራም ነገሮች ሁሉ የሚከለክል ትልቁ መከላከያ ነው 🕌
2️⃣ መጥፎ አጋጣሚዎችንና ቦታዎችን መሸሽ፦ ወደ ሀራም የሚወስዱ መንገዶችን (ማህበራዊ ሚዲያ📱፣ መጥፎ ጓደኞች🚫፣ ወይም አላስፈላጊ ቦታዎች) መራቅ።
3️⃣ ጥሩ ጓደኞችን መያዝ፦ ወደ መልካም ነገር የሚያስታውሱዎትና ወደ አላህ መንገድ የሚወስዶትን መልካም ጓደኞችን መርጦ መያዝ 👫
4️⃣ ዱዓ ማብዛት፦ አላህ ከሀራም ነገሮች እንዲያርቆትና በሐላሉ እንዲያብቃቃዎት በቋሚነት እሱን ይለምኑት 🤲
5️⃣ ጊዜን በጠቃሚ ነገር ማሳለፍ፦ ትርፍ ጊዜዎን መስጅዱ ውስጥ በመሆን 🕌: በቁርዓን📖፣ በትምህርት📚 ፣ በዚክር📿 : በኢስቲግፉር : በስራ🔧 ወይም በስፖርት በማሳለፍ አእምሮዎ ወደ ሀራም እንዳያስብ ማድረግ።
6️⃣ ተውበት ኢስቲግፋር ማድረግን ማብዛት 🔄: በሆነ አጋጣሚ ᵗህተት ቢሰሩ እንኳ ተስፋ ሳይቆርጡ ወዲያውኑ ወደ አላህ ተመልሰው ምህረትን መጠየቅ።
7️⃣ መልካም ስራዎችን አቅሞ በፈቀደው መጠን ማዘውተር 🎯 ለምሳሌ:- ሰላት 🕌 : ጾም ☀️ : ሰደቃ 🤝 : የቀብር ዚያራ : የታመመን መጠየቅ ... ወዘተ
8️⃣ በዚህ መንገድ ላይ መጽናት ትዕግስት ማድረግ ዋናው ቁልፍ ነው 🔑

ያ አላህ በሀቅ መንገድ ላይ አጽናን 🤲
ያ አላህ ከሀራም መንገድ አርቀን
ያ አላህ ዱንያ አኼራችንን አሳምርልን 🌍

ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ
❤22
August 10, 2026 3.5K 30