Diinii kee Anaakara (Md Ali): post #4675 — TG.ME

የማለዳ መልእክት (46)
~
ከአቡ ሁረ ይረህ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ተይዞ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

أكْملُ المؤمنينَ إيمانًا أحسنُهُم خلقًا . وخيارُكُم خيارُكُم لنسائِهِم

"ከምእመናን መካከል ኢማኑ ሙሉ የሆነው ሥነ-ምግባሩ ያማረው ነው። ከእናንተ መካከል በላጮቹ ለሴቶቻቸው (ለባለቤቶቻቸው) መልካም የሆኑት ናቸው።"

[አቡ ዳውድ (4682)፣ ቲርሚዚይ (1162) እና አሕመድ (2/ 472) የዘገቡት ሲሆን ሸይኹል አልባኒይ "ሐሰኑን ሶሒሕ" ብለውታል። (ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 1162) ]

የራሳችንን ሁኔታ እናጢን፤ የተሻለ ለመሆንም እንጣር።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 01/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
August 14, 2026 198