ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ልዩ ሥጦታ ተበረከተላቸው
___
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) በቅርቡ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ዛሬ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ደቀ መዛሙርቱን በሚያስመርቅበት ወቅት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ገበታው የወርቅ ቅብ የሆነ የቅዳሴ መጽሐፍ ተበርክቶላቸዋል።
በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት የበላይ ሓላፊ በራሳቸው እንዲሁም በሚዲያው በኩል የተለያዩ ሥጦታዎችን ሠጥተዋል።
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት
4July 4, 2026 1.5K





