Hamza School/ሐምዛ ት/ቤት: post #2703

ጉዳዩ እርዳታ ጥሪን ይመለከታል
በቅድሚያ የከበረ ሰላምታችንን እያቀረብን ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው የት/ቤታችን የተማሪዎች ወላጅ አቶ አብዱላሂ አሊ ግራር አካባቢ በተፈጠረው የሚኖርበት ፎቅ መደርመስ አደጋ በቤተሰቡ ላይ የሞት እና ከፍተኛ የመቁሰል አደጋ አጋጥሞታል ሟች ልጁ ሙሀመድአሚን አብዱላሒ በ2016 ት/ዘመን 8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት በማስመዘገብ ከ2017 ት/ዘመን ጀምሮ በአደጋው ሕይወቱ እስካለፈበት እለት ድረስ በመወዳ ት/ቤት ሲማር ነበር:: በመሆኑም ከአደጋው የተረፈ ምንም ንብረት ስለሌለ እና ስለወደመበት በተጨማሪም ቀሪ በህክምና ላይ ያሉ ቤተሰቦቹን ለመርዳት እንደትምህርት ቤት እንቅስቃሴ ጀምረናል ውድ ወላጆች አቅማችሁ የፈቀደውን ለተረፉት ቤተሰቦች መቋቋሚያ እና ለህክምና የሚሆን ገንዘብ ትልኩልን ዘንድ በ አላህ ስም ጥሪያችንን እያስተላለፍን ለምታደርጉት ትብብር ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን::
❤24👍9🕊2