👉🏿 ብርሃን ካለ … ጨለማ ሊኖር አይችልም!
1. ፍቅር ካለ … ጥላቻ ሊኖር አይችልም!
2. ትዕግስት ካለ … ቁጣ / ንዴት ሊኖር አይችልም!
3. ይቅርታ ካለ … ቂም / በቀል ሊኖር አይችልም!
4. መስጠት / ማካፈል … ካለ ስግብግብነት ሊኖር አይችልም!
5. ደስታ ካለ … ሀዘን ሊኖር አይችልም!
6. የዋህነት ካለ … ክፋትና ተንኮለኝነት ሊኖር አይችልም!
7. እውነተኝነት ካለ … ግብዝነት ሊኖር አይችልም!
8. ቅንነት ካለ … ቅናትና ምቀኝነት ሊኖር አይችልም!
9. መባረክ ካለ … መራገምና ስድብ ሊኖር አይችልም!
10. ሰላም ካለ … ጠብ ሊኖር አይችልም!
11. እምነት ካለ … ፍርሃት ሊኖር አይችልም!
12. ትህትና ካለ … ትዕቢት ሊኖር አይችልም!
ጨለማን የምናጠፋው ብርሃን እንዲኖር በማድረግ ብቻ ነው! የማንፈልጋቸው ነገሮች እንዳይኖሩ ከመታገል ይልቅ መኖር የሚገባቸው ነገሮች እንዲኖሩ የብርሃኑን ምንጭ እንከተል! ምንጩም ኢየሱስ ብቻ ነው!
----
ዩሐ8: 12 ደግሞም ኢየሱስ፡— እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።
ዩሐ1: 4 - 5 በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም።
Halwot Worship Ministry
21
1
1January 28, 2026 1.7K 4