አህመዲን ጀበል "በቱፋ ላይ ስህተቱ የተከሰተው ከደስታ ብርታት የተነሳ ነው" ብሎ ለሞገተበት የተሳሳተ ፅሁፍ የተሰጠ ገላጭ የሆነ ምላሽ!!
—————
ሸይኽ ጧሀ ኸድር አል-ጂሚ (ሀፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ:-
ከአህመዲን ጀበል ስህተት የመጅሊሳቸው መሪ ቱፋ የነቢይነትን መዕረግ ለመስጠት የተጣጣረበትን ስህተት በሚዛናዊነት ግርዶሽ ከደስታ ብዛት የተሳሳተ ለማስመሰል መሞከሩ ነው። አስቀያሚ የሆነን መንገድ በመጓዝ በፈጣጣነት ያለ ሀፍረት "ከደስታ ብዛት ነው የተሳሳተው" በማለት በእራሱ ላይ በመሀይምነቱ ፈርዷል። ይህ ደግሞ ግልፅ የሆነ ውሸት ነው፣ የመጅሊሱም መሪ ይህን አይሞግትም የአዕምሮ ባለቤት የሆነውም ሰው የሚቀበለው ነገር አይደለም።
1, ከነቢዩ ﷺ የመጣው "ከደስታ ብዛት ተሳሳተ" የሚለው ሀዲስ፣ አላህ ጥላው የጠፋችውን ግመሉን ስለመለሰለት በዋለለት ፀጋ አላህን ማመስገንና ማላቅ ፈልጎ ነው ምላሱ የቀደመው። እንዲህ ያለው ነገር ደግሞ በድንጋጤ አለያም በደስታ በአንድ ወይም በሁለት ቃላት በምላስ መከርበትና የቃላት ቦታ መለዋወጥ ምክንያት ሊከሰት የሚችል ነው።
ይህ ደግሞ ከመጅሊስህ መሪ በተቃራኒ ነው፣ የመጅሊስህ መሪ በሙሉ አገባብና አውዱን የጠበቀ የቃላት አሰካክ ተጠቅሞ ነው ይህን ቃል የተናገረው። ደስታውም ለሰዎች ከመከቱ'ል ሙከረመህ እንደምትክ ሆኖ ለሀጅ ጉዞ እንዲያገለግል ታቅዶ በተሰራ ስፍራ ነው።
2, ሌላው በሀዲስ የመጣው "ከደስታ ብዛት የተነሳ የተሳሳተው" ትክክለኛ ነገር ሊናገር ፈልጎ ነው እንጂ ቀድሞውኑ ስህተት ሊናገር አልነበረም።
3, ይህ ባሪያ ከሚፈልገው በተቃራኒ የተከሰተ የምላስ ወለምታ ነው፣ ይልቁንም ባሪያው የፈለገው ከመጅሊስህ መሪ በተቃራኒው ነበር። ለመሆኑ ጠ/ሚሩን የነቢይነት ማእረግ እንደሚገባው ከመናገር ተቃራኒ ነበር የፈለገበት? ለዚያ ነው እንዴ መልክተኝነት (ነቢይነት) ስለተደመደመ ወሊይነት ይገባሃል ያለው? አንተ የአደም ልጅ አዕምሮ ባለቤት ሆይ! እዚህ ጋር መናገር የፈለገው ከዚህ ሌላ ሆኖ ሳለ የተሳሳተው ቃል አለን? በተለይ የመጅሊሱን መሪ ንግግር ያደመጣችሁ የኦሮሚኛ ተናጋሪዎች ሆይ! እስቲ ንገሩን?
4, በተለምዶ የሰዎችን ሁኔታዎች በማወቅ ልምድ ያላቸው የፍርድ ቤት ዳኞች አንድ ሰው በሆነ ጥፋት ላይ በተደጋጋሚ በመውደቁ ምክንያት በድጋሚ ጥፋት ላይ ሲያገኙት "የፈለግኩበት ሌላ ነው… አስቤበት አይደለም…" ብሎ ሲሞግት ጥፋት ላይ የወደቀው የምር ድንገት ሳያስብ አምልጦት ይሁን አይሁን በጥንቁቅነቱና ባለው ራሱን መቆጣጠር ያውቁታል፣ የምር እንደሞገተው ከሆነ ይቀበሉታል፣ አለያ ግን ውድቅ ያደርጉበታል። [ይህን ዒራቂ የተናገረው ሲሆን አል-ወለዊይም ተቀብሎ በማንሳት አፅንቶታል]
ከዚህ አንፃር ደግሞ የመጅሊስህን መሪ ተጨባጭ ስናየውና ከርሱም የተለመደው ነገር፣ ሸሪዓን በሚፃረር ነገር ላይ መውደቁ ራፊዷዎችን መርዳቱንና ለእነሱም አጋርነቱን መግለፁን ይመስል…፣ ለዲናዊ ጉዳይ ምንም ቦታ አለመስጠቱ… ይህን መከላከልህንና ምክንያቱን እያወቀ የተጋለጠው አካል ሊያጠራህ ፊቱን ወዳንተ አላዞረም። እወቅ ይህ ለዲን ካለህ የሳሳ ግንዛቤ መሆኑ ነው።
አል-ኢማም ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- “ለዚያም ነው አላህ ጥራት ይገባውና ግመሉ ጠፍቶበት ተስፋ ከቆረጠ በኋላ በመገኘቱ የተነሳ ከደስታ ብዛት የተሳሳተውን ሰው ያልያዘው፣ ሲያገኛት ከደስታ ብዛት "አላህ ሆይ! አንተ ባሪያዬ ነህ እኔ ጌታህ ነኝ" ብሎ የተሳሳተው፣ ይህ ቃል ሳያስበው ድንገት በምላሱ ተከሰተ፣ በመሆኑም አላህ በዚህ አልያዘውም፣ ይህ ደግሞ አንድ ቁርኣን የሚቀራ ሰው ድንገት በምላሱ ላይ እንደሚፈጠረው የምላስ ወለምታ ነው።" እንዲህም አሉ:- "የባሪያው የምላስ ፍጥነት ከሚያስበው ተቃራኒ የሚከሰት የምላስ ወለምታ ይሆናል።"
ኢብኑ ሐጀር (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:- "አንድ ሰው በሆነ ነገር ላይ መናገር ይፈልግና ምላሱ ይቀድመዋል…"
ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- "ፈጥኖ ምላሱ በተናገረው ስህተት አይያዝም፣ ምክንያቱም ይህ ከርሱ የተገኘው ንግግር ይህ ሰው ሳያስበው የተናገረው ነው፣ ይልቁንም በምላሱ ቀድሞት ነው የተከሰተውና ከደስታ ብዛት የተሳሳተው። እንዲህ ያለው የምላስ ወለምታ ሰዎችን አይጎዳም፣ ምክንያቱም አስቦበት ስላልሆነ። ሆነ ተብሎ ታስቦበት የሚነገርን ንግግርና ሳይታሰብበት ድንገት በምላስ ወለምታ ምክንያት የሚከሰትን ንግግር መለየት ግድ ይላል።"
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#Join ⤵️⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
Follow Ibn Shifa's WhatsApp Channel: ⤵️⤵️ https://whatsapp.com/channel/0029VbAU7moHgZWXXXnNiL3f