ትንታ
ቁርስ፣ ምሳ ወይም እራት እየተመገብን በድንገት እናንተም ሆናችሁ አጠገባችሁ ያለ ሰው ትንታ ሲያጋጥመው ግራ በመጋባትና በድንጋጤ ሆነን "አረ ቶሎ ውሃ ስጡት !" ፣ "አፉ ውስጥ እጃችንን ከተን እናውጣው!" እያልን እንጯጯሃለን።
ነገር ግን እውነት ለመናገር እነዚህ የምናደርጋቸው የተሳሳቱ እርምጃዎች ነገሩን አባብሰው ጉሮሮው ላይ ያለውን ነገር ይበልጥ ወደ ውስጥ ማለትም ወደ አየር ቱቦ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ህይወትን በአጭር ጊዜ ውስጥ አደጋ ውስጥ ሊከት ይችላል።
ስለዚህ ዛሬ ሁላችንንም ሊጠቅመን የሚችለውን ትክክለኛና ፈጣን የትንታ የመጀመሪያ እርዳታ በአጭሩ ይዤ መጥቻለው
📌 ይህንን እጅግ ጠቃሚ መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ 'Share' በማድረግ የሰዎችን ሕይወት ከድንገተኛ አደጋ እንጠብቅ! 🏥❤️
🚨 ጉሮሮ ውስጥ ባዕድ ነገር ወይም ምግብ ሲቀረቀር /Choking/ ሲፈጠር ምን ማድረግ አለብን? 🚨
✅ እነዚህን ቀላል ግን ወሳኝ እርምጃዎች ማወቅ የሰውን ህይወት በሰከንዶች ውስጥ ከሞት ሊታደግ ይችላል፦
🛡 1. በደንብ እንዲያስል ንገሩት።
ሰውዬው ማሳል የሚችል ከሆነ በጭራሽ አትደናገጡ፤ አብረዋችሁ ሆነው በኃይል እንዲያስል አበረታቱት። ምክንያቱም ተፈጥሯዊው ማሳል ጉሮሮ ውስጥ የተቀረቀረውን ነገር በራሱ ወደላይ እንዲወጣ ለማድረግ ትልቁ መፍትሄ ነው።
👊 2. የጀርባ ምት ዘዴን (Back Blows) ተጠቀሙ ።
ሰውዬውን ትንሽ ወደፊት ዘንበል አድርጉትና በእጅዎ መዳፍ በሁለቱ ትከሻዎች መሀል ወደ መሬት አቅጣጫ አድርጋችሁ 5 ጊዜ በሃይል ምቱት ይህን ስላችሁ ደሞ ግደሉት እያልኩ አይደለም የተቀረቀረው ባዕድ ነገር ወይም ትን ያለውን ምግብ ለማውጣት ነው እንጂ ።
🔄 3. የሄምሊክ ማኑቨር (Heimlich Maneuver) ዘዴን ተግብሩ:
ከሰውዬው ጀርባ ቁሙና ፤ እጆችዎን በሆዱ ዙሪያ (ከእንብርት በላይ እና ከ እንብርት በታች) አክብቡት። ከዛ ኃይልን በመጠቀም ወደ ውስጥ እና ወደላይ (In and Up) አድርገው 5 ጊዜ ይጫኑት (ግፉት)።
ዕቃው ወጥቶ አየር እስኪከፈት ወይም እርዳታ እስከሚደርስ ድረስ ይህንን ዘዴ ይጠቀሙ ።
🛑 በፍጹም መደረግ የሌለባቸው አደገኛ ስህተቶች! 🛑
🚫 ሰው ትንታ ሲያጋጥመው ውሃ መስጠት፦ ይህ ፈፅሞ ስህተት ነው ምክንያቱም የአየር ማስተላለፊያ ቱቦው ሙሉ በሙሉ በተዘጋበት ሰዓት ውሃ ማጠጣት ፈሳሹ በቀጥታ ወደ ሳንባ የመግባት (Aspiration) አደጋ ያጋልጠዋል
🚫 አፉ ውስጥ በእጅ በማስገባት ለማውጣት በጭራሽ እንዳትሞክሩ፦ ጉሮሮው ላይ የተቀረቀረው ምግብ ወይም ባዕድ ነገር አይወጣም፤ ይልቁንም ወደ ውስጥ በደንብ እንዲገባና ሁኔታውን እንዲባብሰው ያደርጋል።
🚫 ደንግጣችሁ ዝም ማለት የለባችሁም፦ ሰውዬው መናገር አቅቶት አንገቱን በእጁ ይዞ ሲታፈን እያያችሁ ዝማ ማለት የለብዎትም፤ ወዲያውኑ እርዳታ ይጀምሩ።
📚 መረጃው የተወሰደባቸው ምንጮች
- World Health Organization (WHO):Guidelines on Choking and Airway Management
- American Red Cross / Mayo Clinic :First Aid for Choking and Heimlich Maneuver
በረከት ከፈነ: የቀዶ ህክምና ነርስ
@HakimEthio
38
11
4August 29, 2026 5.2K 1 30



