የበረሃው እንባ
ክፍል 28
ፀሐፊ ✍️zoya...
ዶክተሩ ከኦርሳም ጋር እያወራ ነው
አእምሮዋ ሙሉ በሙሉ አልጠፋም የድሮ ትዝታዋ ጥልቅ ክፍል ውስጥ ገና አልሞተም አንተን የማስታወስ ትልቅ ጭላንጭል አለ" አለው ዶክተሩ።
ኦርሳም ይሄን ሲሰማ በሃዘን ባህር ውስጥ እያለ የብርሃን ጭላንጭል የታየው መሰለው ለአፍታ መተንፈስ አቃተው ሳይዘገይ የክፍሉን በር በእርጋታ ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ ሳቢራና ያቺ በጎ አድራጊ የጎዳና ተዳዳሪ ሴትዮም ተከተሉት
ሀኪያ በነጩ አልጋ ላይ ተኝታለች አይኖቿ ተከፍተዋል ነገር ግን አሁንም ያው ባዶ እይታ ነው ኦርሳም በአልጋዋ አጠገብ ተንበርክኮ ደረቅ ያሉትን እጆቿን በሁለት እጆቹ በጥብቅ ጨበጣቸው
"ሀኩዬ... እኔ ነኝ ወንድምሽ ኦርሳም" አለ ድምፁ እየተንቀጠቀጠ "አልሞትኩም መጥቻለሁ እሙ ወደ እኔ ልካሻለች... አሁን ብቻሽን አይደለሽም።"
ሀኪያ የኦርሳምን ድምፅ ስትሰማ፣ ያ ባዶ አይኖቿ ቀስ ብለው ተንቀሳቀሱ ወደ ኦርሳም ፊት ትኩር ብላ አየች በአይኖቿ ማዕዘን ላይ አንዲት የፈሰሰች እንባ ተንከባለለች... ከንፈሮቿ ተንቀጠቀጡ
ኦርሳም ተስፋ ሳይቆርጥ የእህቱን እጅ ወደ ጉንጮቹ እያስጠጋ በሃዘን አያት ሳቢራም ከአጠገቡ ተንበርክካ የሀኪያን ሌላኛውን እጅ ይዛ በሰላም አበሰችው በዚህ ቅጽበት በክፍሉ ውስጥ የነበረው ድባብ የዓመታት ስቃይንና እንባን የሚፈውስ ይመስል ነበር።
በቀጣዮቹ ቀናት ኦርሳም እናቱን ጀሚላን ያጣበትን መርዶ በቅንነት ተቀብሎ ስርአተ ቀብሯ የተፈጸመበትን ቦታ በአካባቢው ሰዎች እርዳታ አፈላልጎ አገኘ ሳቢራንና ያቺን የጎዳና ተዳዳሪ ሴትዮ ሀኪያ ጋር አስቀምጦ ወደ እናቱ መቃብር አመራ። መቃብሩ ላይ ተደፍቶ የዓመታት ናፍቆቱን በስደት ያየውን መከራና የዛሬውን ስኬት በእንባ አወጋት "እማዬ የኔ ውድ ሕልምሽን እየኖርኩ ነበር አንቺ ብትኖሪ ሁሉም ነገር ውብ ይሆን ነበር ... አደራሽን ተቀብያለሁ ሀኪያን አግኝቻታለሁ እስከ መጨረሻው እስትንፋሴ ድረስ እጠብቃታለሁ" ሲል ቃል ገባላት።
የእናቱን ሃዘን ከልቡ ካስቀመጠ በኋላ ኦርሳም ሙሉ ትኩረቱን ወደ እህቱ ህክምና አዞረ አዲስ አበባ ውስጥ ያሉትን ምርጥ የነርቭና የስነ-አእምሮ ስፔሻሊስቶች አነጋገረ ነገር ግን የሀኪያን አእምሮ ሙሉ በሙሉ ለመመለስና የተሻለ ህክምና ለመስጠት ወደ ውጭ አገር መውሰድ እንዳለበት ዶክተሮቹ መከሩት።
ኦርሳም ወደ ጣሊያን ተመልሶ እህቱን ማሳከም የሚችልበትን መንገድ ማመቻቸት ጀመረ ለዓመታት የደከመበትን የጣሊያን ቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ ተጠቅሞ ለሀኪያ እንዲሁም በችግር ቀን ያልተለየቻቸውን ያቺን የጎዳና ተዳዳሪ ሴትዮ ጭምር የጉዞ ሰነዶችን ማዘጋጀት ጀመረ
ይሁንና ሀኪያ አሁንም ሙሉ በሙሉ አልነቃችም አልፎ አልፎ አይኖቿ ላይ የሚታየው የፍርሃትና የመባነን ስሜት ኦርሳምን ክፉኛ ያስጨንቀዋል
የጉዟቸው ቀን ተቃረበ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም የሚበረው አውሮፕላን ውስጥ ለመግባት ጥቂት ቀናት ሲቀሯቸው በአንድ ምሽት ሆስፒታል ውስጥ ኦርሳም ከሀኪያ አልጋ አጠገብ ተኝቶ ሳለ በክፍሉ ውስጥ ያልተለመደ ድምፅ ተሰማ
ኦርሳም ደንግጦ ሲነቃ ሀኪያ ከአልጋዋ ላይ ተነስታ ቁጭ ብላለች። አይኖቿ ፍርሃት ተሞልተዋል ወደ መስኮቱ እየተመለከተች እጆቿን ዘርግታለች።
በውጪው አስፓልት ላይ የሚሄዱትን የመኪና መብራቶች ስታይ የድሮው አደጋ በአእምሮዋ ላይ በድጋሚ ያንቀጠቀጣት መሰለ
ከአልጋዋ ላይ ወርዳ ወደ መስኮቱ ልትሮጥ ስትል ኦርሳም በፍጥነት ተነስቶ አቀፋት "ሀኩዬ... እኔ አለሁ አትፍሪ" እያለ አጥብቆ ያዛት
ሀኪያ በኦርሳም እቅፍ ውስጥ ሆና ክፉኛ ተንቀጠቀጠች ከዚያም ለመጀመሪያ ጊዜ የኦርሳምን ፊት ትኩር ብላ አየችውና በሚያስደነግጥ ጩኸት...
ኦርሳም...!" ብላ ጮኸች። ያ ድምፅ ከጉሮሮዋ የጠፋ የመሰለና ለዓመታት የታፈነ፣ የናፍቆትና የፍርሃት ድብልቅልቅ የነበረበት ጩኸት ነበር።
ኦርሳም አፉን ከፍቶ ስሙን ስትጠራው ጆሮውን ማመን አልቻለም የልቡ ትርታ በአንዴ ጨመረ ከዓይኖቹ የደስታ እንባዎች ይፈስሱ ጀመር።
.
"ሀኩዬ... አዎ እኔ ነኝ ወንድምሽ ነኝ!" እያለ ይበልጥ ወደ ደረቱ አስጠጋት።
ሀኪያ የኦርሳምን ፊት በሁለቱ እጆቿ ዳሰሰችው አይኖቿ ውስጥ የነበረው ያ ባዶና የራቀ እይታ እየጠፋ፣ የማወቅና የማስታወስ ብርሃን እየተተካ መጣ። "ኦርሳም... እውነት አንተ ነህ አልሞትክም?" አለች ድምጿ እየተንቀጠቀጠ "እማዬ እኮ... እማዬ እኮ በየቀኑ ታለቅስ ነበር ባህር ላይ ቀርቷል እያለች..." ንግግሯን ሳትጨርስ የእናቷ የጀሚላ በአደጋ የመሞት ትዝታ በአእምሮዋ ላይ እንደ መብረቅ ብልጭ አለባት
"እማዬስ? እማዬ የት ናት?" እያለች አካባቢዋን በድንጋጤ መቃኘት ጀመረች መኪናዎቹ መብራቶቹ፣ ያ አስፓልት ላይ የፈሰሰው ደም ሁሉ ትዝ አላት። እንደገና ልትባንንና ልትጮህ ስትል ኦርሳም ግንባሯን ሳማትና "ሀኩዬ... ተረጋጊ፣ አሁን መከራው አልፏል። እኔ አጠገብሽ አለሁ። እማማ አሁን ሰላማዊ ቦታ ናት ያለችው" እያለ ሊያረጋጋት ሞከረ
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀኪያን ጩኸት ሰምተው ሳቢራ፣ የጎዳና ተዳዳሪዋ ሴትዮና ዶክተሩ በፍጥነት ወደ ክፍሉ ገቡ ሀኪያ ተቀምጣ ከኦርሳም ጋር ስታወራ ሲያዩ ሁሉም በድንጋጤና በደስታ ደረቁ።
ዶክተሩ በፍጥነት ቀርቦ የሀኪያን አይኖችና የልብ ትርታ መረመረ "ይህ ተአምር ነው" አለ ዶክተሩ በደስታ ፈገግ ብሎ "ያ የተቆለፈው የአእምሮዋ ክፍል በወንድሟ ድምፅና እቅፍ አማካኝነት ተሰብሯል ትዝታዎቿ ሙሉ በሙሉ እየተመለሱ ነው፣ ነገር ግን አሁንም ከፍተኛ ጥንቃቄና እረፍት ያስፈልጋታል።"
ያቺ የጎዳና ተዳዳሪ ሴትዮ ሀኪያ ስትናገር ስታይ ተንበርክካ ማልቀስ ጀመረች ሀኪያ ወደ እሷ ዞራ አየቻትና፣ "አንቺ... አንቺ እኮ ሁልጊዜ የምትጠብቂኝ ሴትዮ ነሽ" አለች የአመስጋኝነት ስሜት በፊቷ ላይ እየታየ ሴትየዋም "አዎ ልጄ... አሁንማ ወንድምሽ መጣልሽ ጨለማው አበቃ" አለቻት
ሳቢራም ወደ አልጋው ተጠግታ የሀኪያን እጅ ያዘች።ኦርሳም ወደ ባለቤቱ ዞሮ"ሀኩዬ... ይህቺ ባለቤቴ ሳቢራ ናት በችግሬ ጊዜ አብራኝ የነበረች፣ አንቺን እንድፈልግ ብርታት የሆነችኝ" ሲል አስተዋወቃ ሀኪያ ሳቢራን እቅፍ አድርጋ አነባች
በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የሀኪያ አእምሮም ሆነ አካል በከፍተኛ ሁኔታ አገገመ የእናቷን መርዶ በዝምታና በሃዘን ብትቀበለው፣ ወንድሟ ኦርሳም ከጎኗ መሆኑ የተሰበረ ልቧን ጠገነው
የጉዟቸው ቀን ደረሰ ኦርሳም፣ ሳቢራ፣ ሀኪያ እና ያቺ የጎዳና ተዳዳሪ ልጅ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኙ ኦርሳም በግርምት ሳቢራን አያት የጎዳና ተዳዳሪዋ ሴት በጣም ውብ እና ስትታይ እድሜዋ ከሀኪያ እድሜ ጋር ሚቀራረብ ይመስላል ። ኦርሳም ወደ ኋላው ዞሮ አዲስ አበባን በአይኖቹ ተሰናበታት። ይህች ከተማ የእናቱን ህይወት ብትወስድበትም የተረፈችውን እህቱን ግን መልሳለታለች ።
አውሮፕላኑ ከመሬት ተነስቶ ወደ ሰማይ በረረ ኦርሳም በአንድ እጁ የሳቢራን በሌላ እጁ ደግሞ የሀኪያን እጅ አጥብቆ ያዘ ከፊታቸው አዲስ ህይወት፣ አዲስ ተስፋና በጣሊያን ምድር የሚደረግ የደስታ ዘመን ይጠብቃቸዋል ኢዘድንም በዊልቸር ቢሆንም ጥሩ ሕይወት ጣልያን ውስጥ እየኖሩ ነው ።
የበረሃውና የባህሩ እንባ አብቅቷል አሁን የፈገግታ ጊዜ ነው።
.......
.......
............
ከ 100🥰 ቡሃላ .......
☆#ቀጣይ_ክፍል__ይቀጥላል☆....
156
5
1October 2, 2026 2.7K 1 13