የበረሃው እንባ
ክፍል 25
ፀሐፊ ✍️ zoya~
"ምን ሀኪያም አብራ ነው የጠፋችው?" የኦርሳም ድምፅ መላውን ሰፈር አናወጠው የሰማዩ ፀሐይ በላዩ ላይ ክፉኛ የጋለች መሬቱም የምታንቀጠቅጠው መሰለው
ያቺ አፏን በነጠላዋ የሸፈነችው ጎረቤት እንባዋ እየፈሰሰ ቀጠለች "አዎ ልጄ... እናትህ ጀሚላ ብቻዋን አልነበረችም በፌስታል የያዘችውን የሬድዮ ማስታወቂያና የልመና ወረቀት ይዛ ሀኪያን በጋሪ እያስገፋች ነበር የሄደችው ከዚያ በኋላ ግን እናትህንም ሆነ እህትህን ያያቸው አንድም ሰው የለም።"
ኦርሳም የለበሰውን ጥቁር ሱፍ ሳያግደው እዚያው አቧራው ላይ ተዘረረ በሁለት እጆቹ መሬቱን እየቧጨረ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ "እሙ... ሀኩዬ... ይሄን ሁሉ መከራ ስታዩ ምን እሰራ ነበር ለምን ተረፍኩ ለምንስ መጣሁ ?" እያለ ራሱን ይወቅስ ጀመር።
የሰፈሩ ሰው ሁሉ የኦርሳምን ስቃይ ማየት አቅቶት አብሮት ይንሰቀሰቅ ነበር ሳቢራ ግን የባሏን ልብ ስብራት ስታይ፣ ከተቀመጠበት አቧራ ላይ ተንበርክካ በትከሻው አቀፈችው የራሷን እንባ እየጠረገች "ኦርሳም... ተነስ የኔ ፍቅር አሁን ማልቀሻ ጊዜ አይደለም" አለችው በለሰለሰና በቁርጠኝነት በተሞላ ድምፅ "አላህ በህይወት ያተረፈህ እንድታለቅስ አይደለም አሁኑኑ ፍለጋ መጀመር አለብን እኔ ካንተ ጎን ነኝ እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ አብሬህ እፈልጋቸዋለሁ"
የሳቢራ ቃላት በኦርሳም ውስጥ አዲስ ብርታት ፈጠሩ አቧራውን አራግፎ ተነሳ አይኖቹ በለቅሶ ቀልተዋል፣ ነገር ግን አሁን ፍርሃት የለበትም
ወደ አቶ ሸሪፍ ዞሮ "አባቴ... የትኛው ሬድዮ ጣቢያ እንደሄዱ ታውቃላችሁ? ወይም የት አካባቢ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚገምት ሰው አለ?" ሲል ጠየቀ
አቶ ሸሪፍ "ልጄ የሄዱት ወደ ዋናው ብሔራዊ ሬድዮ ጣቢያ እንደሆነ አውቃለሁ ከዚያ ውጪ ግን አዲስ አበባ ሰፊ ናት የት እንደወደቁ አናውቅም" አሉት
ኦርሳም ወደ መኪናው አመራ ሳቢራም አብራው ገባች ከሰፈሩ ሰዎች ጋር ተሰናብተው የእናቱንና የእህቱን ፈለግ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባው ግርግር ውስጥ ገቡ።
መጀመሪያ ያመሩት ወደ ሬድዮ ጣቢያው ነበር እዚያ ለዓመታት የሰሩ ጋዜጠኞችንና ሰራተኞችን ለማግኘት ሞከሩ ነገር ግን ከስድስት ዓመት በፊት የተደረገን የልመና ጥሪና ማስታወቂያ ማህደር ፈልጎ ማውጣት ከባድ ነበር ኦርሳም ግን ተስፋ አልቆረጠም ለጣቢያው ሰራተኞች የሚስቱንና የራሱን ታሪክ ነግሮ የገንዘብ ሽልማት ጭምር በመመደብ ልዩ ማስታወቂያ በድጋሚ እንዲነገር አደረገ።
"ወይዘሮ ጀሚላ እና ልጅዎ ሀኪያ የትም አላችሁበት... ልጅሽ ኦርሳም በህይወት አለ ከጣሊያን መጥቶ ይፈልጋችኋል..." የሚለው ጥሪ በአየር ላይ ተለቀቀ
ቀናት ወደ ሳምንታት ተቀየሩ ኦርሳምና ሳቢራ በየቀኑ ከአንዱ መጠለያ ወደ ሌላው መጠለያ ከአንዱ ሆስፒታል ወደ ሌላው ሆስፒታል ይዞራሉ የአዲስ አበባን አውራ ጎዳናዎች የልመና ቦታዎችን ሁሉ አበጠሩ
አንድ ምሽት በጣም ደክሟቸው ሆቴል ውስጥ ተቀምጠው ሳለ የኦርሳም ስልክ ጠራ የማያውቁት ቁጥር ነበር
ኦርሳም ልቡ እየመታ ስልኩን አነሳው "ሄሎ..."
ከመስመሩ ማዶ አንድ ሰው ጎርናና ድምፅ ተሰማ "ሄሎ... ኦርሳም የምትባለው አንተ ነህ በሬድዮ ስለ እናትህ ጀሚላና ስለ እህትህ ሀኪያ የምታስፈልገው?"
ኦርሳም ደረቱን ያዘ "አዎ እኔ ነኝ እባክህ የምታውቀው ነገር አለ?"
"ከሦስት ዓመት በፊት እኔ በምሰራበት የአዕምሮ ህክምና ማእከል እና በአካባቢው ባለ መጠለያ ውስጥ..."
ሰውየው ንግግሩን ሳይጨርስ ኦርሳም ከአልጋው ላይ ብድግ አለ "እባክህ ወንድሜ... እባክህ የምታውቀው ነገር ካለ ንገረኝ አድራሻውን ስጠኝ" አለ ድምፁ እየተንቀጠቀጠ ሳቢራም የባልዋን መደናገጥ አይታ ከአጠገቡ ተቀመጠችና እጁን አጥብቃ ይዛው ማድመጥ ጀመረች
ሰውየው በረዥሙ ተነፈሰና "የኔ ጌታ እኔ እዚያ ማዕከል ውስጥ ጥበቃ ነኝ በሬድዮ የተላለፈውን ማስታወቂያ ስሰማ ነው ትዝ አላችሁኝ። አንዲት ልጅ... አዎ አንተ ያልካት ሀኪያ ይመስለኛል እሷን እዚያው አካባቢ ያሉ የበጎ አድራጎት ሰዎች ወስደዋታል አሁን የት እንዳለች እርግጠኛ ባልሆንም በአቃቂ አካባቢ ባሉ መጠለያዎች ሳይሆን አይቀርም" አለው
ኦርሳም ይሄን ሲሰማ በትንሹም ቢሆን የብርሃን ጭላንጭል ታየው ስልኩን እንደዘጋ ወደ ሳቢራ ዞሮ "ሳቢራ... ሀኪያን አድራሻ አግኝተናል አቃቂ መሄድ አለብን" አለ ሳቢራም የባልዋን እጅ አጥብቃ ይዛ "አየህ ኦርሳም... አላህ ዱዓችንን ሰምቷል
አለችው ሳቢራ አይኖቿ በደስታና በተስፋ እያበሩ
ኦርሳም ግን በደስታና በጭንቀት መካከል ሆኖ ይርገበገባል መኪናውን አስነስቶ አሁኑኑ ወደ አቃቂ ለመጋለብ ቢፈልግም ሰዓቱ በጣም መሽቷል ውጭው በጨለማ ተውጧል ሳቢራ የባሏን ሁኔታ አይታ በትከሻው አቀፈችውና "ውዴ... አሁን በጣም መሽቷል መንገዱም አይታይም ደግሞም ማዕከላቱ በዚህ ሰዓት ዝግ ናቸው ለዛሬ አድረን ነገ ጠዋት ገና ጎህ ሲቀድ እንሄዳለን እባክህ ትንሽ እረፍት አድርግ" ስትል ለመነችው
ኦርሳም ማደሩ ባይዋጥለትም የሳቢራን ምክር ሰምቶ ተስማማ ሆኖም ያቺ ሌሊት ለኦርሳም የዓመታት ያህል ረዘመችበት አልጋው ላይ ወዲያ ወዲህ እያለ የሀኪያን የልጅነት ገጽታ ያቺን ሳቂታ እህቱን እያሰበ እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር አደረ "አላህ ሆይ... ብቻ እሷን በሰላም አሳየኝ" እያለ ሌሊቱን ሙሉ ዱአ አደረ
ነጋ...
የማለዳዋ ፀሐይ ገና የአዲስ አበባን ሰማይ ሳትሞቀው ኦርሳምና ሳቢራ ከሆቴሉ ወጥተው መኪናቸውን ወደ አቃቂ አቀኑ የኦርሳም ልብ ይፈነዳል እጆቹ መሪው ላይ ይንቀጠቀጣሉ ለዓመታት የተለያትን በእሱ ስደት ምክንያት መከራ ያየችውን እህቱን ሊያገኝ ጥቂት እርምጃዎች ብቻ የቀሩት እየመሰለው መኪናውን በፍጥነት ይነዳው ጀመር
አቃቂ ደርሰው ጥበቃው የጠቆማቸውን መጠለያዎች አንድ በአንድ መፈለግ ጀመሩ መጀመሪያ ያገኙት ትልቅ የበጎ አድራጎት ማዕከል ውስጥ ገብተው የሀኪያን ፎቶ ለኃላፊው አሳዩት
ኃላፊው ፎቶውን በትኩረት አይቶ ራሱን በመነቅነቅ "አይ ልጄ... እኛ ጋር እንዲህ አይነት ልጅ አልመጣችም" አላቸው
ኦርሳም አልደነገጠም "ሌላ መጠለያ ይኖራል" በማለት ወደ ቀጣዩ ማዕከል አመሩ በዚያ አካባቢ ያሉትን ሶስትና አራት ትናንሽ የችግረኞችና የሕሙማን መጠለያዎች እያጠኑ ሰራተኞቹንና የበጎ አድራጎት አስተባባሪዎችን ሁሉ ጠየቁ ነገር ግን የትኛውም ቦታ የሀኪያ ፍንጭ አልነበረም
በመጨረሻም ጥበቃው በዋናነት
ወደጠቆማቸውና አእምሮአቸውን ለሳቱ ህሙማን መጠለያ ወደሚሆን አንድ አሮጌ ግቢ አመሩ የኦርሳም ልብ የመጨረሻ ተስፋውን ይዞ ይመታል
የማዕከሉን ዋና አስተዳዳሪ አግኝተው የሀኪያን ፎቶ አሳዩትና የተባለውን ጥበቃ የሰጣቸውን መረጃ ነገሩት አስተዳዳሪው ፎቶውን ደጋግሞ ካየ በኋላ በረዥሙ ተነፈሰ
"አዎ... ይህቺን ልጅ አውቃታለሁ ከሁለት ዓመት በፊት እዚህ ማዕከል ውስጥ ነበረች" አለ አስተዳዳሪው
ኦርሳም "ነበረች?" ሲል ድምፁ ተሰበረ "አሁን የት ናት እባክህ ንገረኝ?"
አስተዳዳሪው በሀዘን አንገቱን ደፍቶ "ልጄ... ልጅቷ አእምሮዋ ስራ አቁሞ ስለነበር እዚህ ማዕከል ውስጥ ሆና ምንም አትናገርም ነበር ነገር ግን ከአንድ ዓመት በፊት... ከተቀመጠችበት ጠፍታ ወጣች እኛም አካባቢውን ሁሉ ብንፈልግም ልናገኛት አልቻልንም። የት እንደደረሰች አናውቅም አሁንም የጠፉ ሰዎች መዝገብ ላይ ነው ያለችው" አለው።
.......
.......
............
ከ 100🥰 ቡሃላ .......
☆#ቀጣይ_ክፍል__ይቀጥላል☆....
98
6
1September 29, 2026 1K 7 9