የጁመዓ ቀን ሱናዎች 🚿 ገላን መታጠብ ፦ የጁመዓን ሶላት ለመስገድ ገላን መታጠብ የነቢዩ ﷺ ፈለግ ነው።
ንጹህ ልብስ መልበስ፦ ካሉን ልብሶች ውስጥ ያማረውንና ንጹሁን መርጦ መልበስ።
ሽቶ መቀባትና ሲዋክ መጠቀም፦ ለወንዶች ሽቶ መቀባትና ጥርስን በሲዋክ መፋቅ።
ሰለዋት ማብዛት፦ በውድ ነቢያችን ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ (اللهم صل وسلم على نبينا محمد)።
ቀድሞ መስጂድ መገኘት፦ የጁመዓ ኹጥባ ሳይጀመር ቀድሞ በመገኘት የጭንቅላት ሰላምንና ምንዳን ማግኘት።
ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ፦ ኢማሙ ኹጥባ በሚያደርጉበት ወቅት በዝምታና በትኩረት ማዳመጥ።
መልካም ጁመዓ!


