የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዒድ አሰጋገድ ስነስርዓት መግለጫ * አሰላሙዓለይኩም… — Gali Ababor Official — TG.ME

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የዒድ አሰጋገድ ስነስርዓት መግለጫ
*

አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ

የተከበራችሁ የአዲስ አበባ ሙስሊም ነዋሪዎች፥ እነሆ የዙል ሒጃ ወር ዘጠነኛው ቀን ላይ ደርሰናል። አላህ አጠቃላይ ዒባዳቸውን ከሚቀበላቸው ባሪያዎቹ ይመድበን፤ አሚን!

በመቀጠል በነገው ዕለት ረቡዕ በሚከበረው የዒደል አድሓ ዋዜማ ላይ እንደመሆናችን መጠን የዒድ አከባበራችንን እና ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትን እና የዒድ አከባበር አስተባባሪ አብይ ኮሚቴን ወክዬ የተወሰኑ መመሪያዎችንና ማስታወሻዎችን ለማስተላለፍ እወዳለሁ።

ይህም ሰባት ርዕሰ ጉዳዮች አሉት። በስራቸውም የተለያዩ ነጥቦችን ይዟል።

የመጀመሪያው ርዕሰ-ጉዳይ ኡድሒያን አስመልክቶ ሲሆን፥
ዒድ ሶላት ከተሰገደ በኋላ ሸሪዓው ባስቀመጠው መልኩ የኡድሒያ እርድ በማከናወን ወደ አላህ ለመቃረብ ጥረት ማድረግን ለማስታወስ የምንወድ ሲሆን፥ አቅም በፈቀደ መልኩ በዙሪያችን ለሚገኙ ሚስኪኖች በማካፈል ስለሚመገቡት ነገር እየተጨነቁ ከመዋላቸው ልንታደጋቸውና ዒዱን በመተጋገዝ መዋል እንደሚገባን እናሳስባለን።

ሁለተኛው ርዕሰ-ጉዳይ የዒድ መስገጃ ቦታዎችን ስለመጠቆም ሲሆን፥ በዋናነት በአዲስ አበባ ስቴዲየምና በዙሪያው የሚሰገድ ይሆናል። በተጨማሪም፥ የቦታ ርቀትን ታሳቢ በማድረግ
አዲስ ከተማ ክ/ከተማ፥ በአወሊያ
ኮልፌ ክፍለ ከተማ፥ በኢማሙ አሕመድ መስጂድ
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ፥ በጋርመንት አደባባይ
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ፥ በዑመሩብኑል ኸጧብ መስጂድ
ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ከተባበሩት አደባባይ እስከ ፔፕሲ አደባባይ ድረስ የሚሰገድ ይሆናል።
የከተማችን ሙስሊም ማህበረሰብ በተቻለ መጠን ወደነዚህ ስፍራዎች ብቻ ዒድ ሶላት ለመስገድ ሊሄድና ተበታትኖ የመስገድ ልማድ የሚቀርበትን አካሄድ እንዲከተል እንነግራለን። ሌሎች ተጨማሪ መስገጃ ቦታዎች ካስፈለጉ በክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች አስተባባሪነትና ፍቃድ ብቻ የሚወሰን ይሆናል።

ሶስተኛ ርዕሰ-ጉዳይ የዒዱ ዕለት ስለሚኖረን የሶላት አሰጋገድ መመሪያን በሚመለከት ይሆናል። በዚህ ስር የሚከተሉትን ነጥቦች ታሳቢ ልናደርግ ይገባል፦
አንደኛ፥ ወደ ዒድ ሶላት መስገጃ ስፍራ ስንመጣም ሆነ በዕለቱ በሚኖረን ውሎ ላይ በተቻለ መጠን ንጹህ ልብስ ልንለብስና ንጽህናችንን ልንጠብቅ ይገባል
ሁለተኛ፥ የኡድሒያ እርድ የሚያርዱ ምዕመናንን እና ርቀትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የዒድ ሶላት የሚሰገደው ከጠዋቱ 2:00 ላይ ስለሆነ በመንገድ ላይ ሊያስረፍዱን የሚገቡ ጉዳዮችን ታሳቢ በማድረግ በማለዳ ወደ መስገጃ ቦታ መምጣትና መገኘት ይጠበቅብናል።
ሶስተኛ፥ ወደ መስገጃ ስፍራ በሚኖረን ጉዞ ላይ የተለያዩ የጸጥታ አካላት ለእኛው ደህንነትና ለሀገራችን ሰላም ሲባል የፍተሻና የጥበቃ ተግባር ስለሚያከናውኑ ከእነርሱ ጋር ተናበን ልንጓዝ እና ለፍተሻና ለመሰል ጉዳዮች ተባባሪ ልንሆን ይገባል። በኛ ላይ ፍተሻ የሚያደርጉት በክፉ ጠርጥረውን ሳይሆን ለእኛው ደህንነት ሲባል ስራቸውን እየሰሩ በመሆኑ የፈገግታ ፊት እና የሰላምታና የምስጋና ቃላት ልንሰጣቸው ይገባል።
አራተኛ፥ የዒድ ሶላቱንና ተያያዥ ፕሮግራሞችን የሚያስተባብሩ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አርማ ያለበትን ፒፕስ የለበሱና ባጅ ያደረጉ የወጣት ኻዲሞችን የመደብን በመሆኑ ለሚነግሩንና ለሚያዙን ነገሮች ቀና ምላሽ ልንሰጥና ተባባሪ ልንሆን ይገባል።
አምስተኛ፥ ወደዒድ ሶላት ቦታ ስንመጣ መያዝ የሚከለከሉ ቁሳቁስ እና ድርጊቶች አሉ።
ስለትነት ያላቸው ብረቶችንና እስኪርቢቶን ጨምሮ ይዞ መገኘት ክልክል ነው።
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ-ዓላማ ውጪ የትኛውንም አይነት ዓለም-አቀፍም ሆነ በሐገር ውስጥ የሚገኙ ባንዲራዎችን፣ የተቋማትና የቡድን አርማዎችን ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው። ክልከላነቱ በጨርቅ መልኩም ሆነ፣ በአልባሳትነት፣ በመገልገያ ቁሳቁስነትና በጌጣጌጥነት መልኩ መሆኑ ለውጥ የለውም።
የትኛውንም አይነት የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ጽሁፍ የሰፈረበት ቲ-ሸርትና ልብስ ለብሶ መገኘት የተከለከለ ነው።
የትኛውንም አይነት የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ጽሁፍ የሰፈረበት የመፈክር ቁስ፣ ወረቀት፣ በራሪ-ወረቀትና መሰል ነገሮችን ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው።
ኢስላማዊ ሸሪዓው ካስቀመጠው አላህን የመዘከር ወይም የማውሳት ድርጊት ውጪ በየትኛውም አይነት የድጋፍ፣ የተቃውሞ፣ ሀገራዊና ዓለም-አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን የመግለጽ፣ ወዘተ መፈክሮች፣ ጩኸቶች፣ ሁከቶችና ረብሻዎች ላይ አስቦበትም ሆነ ለጨዋታ በሚል እሳቤ ማስጀመር፣ መሳተፍ፣ ማጀብ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
እንደሙስሊም ማህበረሰብ ያሉንን በርካታ ጥያቄዎች በተለያዩ መደበኛና ህጋዊ መንገዶች ብቻ ለሚመለከታቸው አካላት በተቋም ደረጃ፣ በቡድን ደረጃና በግለሰብ ደረጃ እየጠየቅንና መጠየቅ ያለብን ሲሆን፥ በዒዱ እለት ግን የመሰባሰባችን ዓላማ ሶላትና ተያያዥ በኢስላማዊ ሸሪዓህ ላይ የተቀመጡ አምልኮዎችን መፈጸም በመሆኑ ከዚህ በዘለለ ወደ ስሜታዊነት፣ ወደ ግብዛዊነትና ወደ ግብግብ የሚያስገባን ምንም አይነት ምክኒያት የለም።
በሌላ እምነት ተከታዮችና በሚጠቀሟቸው የእምነት ተቋማት ላይ ጸብን የሚያጭር ንግግር መናገር እና ተያያዥ ድርጊቶችን መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
ከአካባቢ ንጽህናና ከገጽታ ግንባታ እንደዚሁም አብረን መዘመን ከሚገቡን ነገሮች ጋር አብሮ ለመራመድ ሲባል ካኪ ወረቀትና ጋዜጣ ለመስገጃነት ይዞ መገኘት የለብንም። በተቻለ መጠን ሁላችንም የምንሰግድበትን መስገጃ ምንጣፍ ይዘን ልንመጣ ይገባል።
እንደ ሽቶና መሰል ቁሳቁሶች ፍተሻ ላይ መጉላላትን ስለሚፈጥሩ ባይመጡ ይመከራል።
ስድስተኛ፥ ማንኛውንም ለሰላምና ደህንነት አጠራጣሪ ሁኔታዎችን የተመለከተ ግለሰብ ለጸጥታ አካላትና ለበጎ ፈቃደኛ አስተባባሪዎች እንዲያሳውቅ እናሳስባለን።
ሰባተኛ፥ የተሽከርካሪ ይለፍ ካርድ (Car Pass) የያዙ አሽከርካሪዎች ተሽከርካሪዎቻቸውን በግዮን ሆቴል ግቢ ወይም ወጋገን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ፓርኪንግ ቦታ ያቆማሉ።
ስምንተኛ፥ የተሽከርካሪ ይለፍ ካርድ (Car Pass) ያልያዙ አሽከርካሪዎች ተሽከርካሪዎቻቸውን በአቅራቢያ ባሉ በሚፈቀዱ የማቆሚያ ስፍራዎች ያቁሙ።
ዘጠነኛ፥ በምንጓዝበት ጎዳና እና በምናደርገው የስግደት ሂደት ላይ የኮሪደር ልማት አረንጓዴ ስፍራዎችንና መሰል የልማት ነገሮችን ከማበላሸት ልንቆጥብ ይገባል።

አራተኛ ጉዳይ ከዒዱ እለት አዋዋላችን ጋር የተያያዘ ሲሆን፥
ይህም አላህን የበለጠ በመታዘዝ፣ ክልከላዎቹን በመከልከል እና አላህ ያገራልንን የመደሰቻ መንገዶችን በመጠቀም፣ ያለንን ለተቸገሩ በማካፈል፣ በአንድነት ልናከብር ይገባል።

አምስተኛው ጉዳይ ከዒዱ እለት በኋላ ልንከተለው ስለሚገባ አካሄድ ሲሆን ይህም
በየትኛውም ወቅት፣ ቦታና ሁኔታ ላይ በአምልኳችን ላይ ከመበርታትና ወደ አላህ ለመቃረብ ጥረት ከማድረግ እንዳንዘናጋ እንላለን።

ስድስተኛው ጉዳይ በቅርቡ ስለሚካሄደው ሀገራዊ የመንግስት ምርጫ ሲሆን ይህም
May 26, 2026 2.1K 1