ማስታወቂያ ለNGAT ተፈታኞች
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአገራዊ የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (National Graduate Admission Test - NGAT) ለመፈተን የተመዘገባችሁ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናውን በተመለከተ የሚከተሉትን አስፈላጊ መረጃዎች እንድታውቁ እናሳስባለን።
1. የቀን፣ የሰዓት እና የፈተና ቦታ መረጃ
የፈተና ክፍል ማወቂያ ዝርዝር፦ ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም. ከቀኑ 2፡30 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ዋና መግቢያ በር ላይ ይለጠፋል።
የፈተና መስጫ ቦታ፦ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ።
የፈተና ቀን፦ረቡዕ፣ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም. እና ሐሙስ፣ ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም.
የፈተና መጀመሪያ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ።
2. ማሳሰቢያ
የፈተና መግቢያ ካርድ፦ ከሲስተሙ ማውረድ ስለተፈቀደ፣ በተመዘገባችሁበት የግል አካውንት በመግባት የፈተና መግቢያ ካርዳችሁን አውርዳችሁ ይዛችሁ መገኘት አለባችሁ።
ሕጋዊ መታወቂያ፦ለፈተና ስትመጡ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ መታወቂያ ወይም የፋይዳ መታወቂያ (Fayda ID) ይዛችሁ መገኘት አለባችሁ።
የተከለከሉ ዕቃዎች፦ወደ ፈተና ጣቢያ ሞባይል ስልክ፣ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተር እና ሌሎች የተከለከሉ ዕቃዎችን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው።
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ድህረ-ምረቃ ትምህርት ቤት
Follow us @gatstudy

15August 23, 2026 4.4K 2 7