#ማስታወቂያ ለብሔራዊ ድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች በሙሉ ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም በሐገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው ብሔራዊ የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች የተመደባችሁበትን መፈተኛ ክፍል በዩኒቨርሲቲው የቴለግራም አድራሻ👇 https://t.me/werabeuniversitywru በመግባት ተጭናችሁ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ፈተናው ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከጥዋቱ 1፡30 ጀምሮ የሚሰጥ ሲሆን ሁሉም ተፈታኞች ለፈተና ስትመጡ የሚከተሉትን የፈተና ሕጎች ማወቅ ይኖርባችኋል፡፡ 1.ፈተናው ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በፊት ቀድማችሁ ፈተና አዳራሽ ውስጥ መገኘት አለባችሁ 2.ፋይዳ ወይም ሌላ ማንነታቸሁን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ አለባችሁ 3.የፈተና መግቢያ ቲኬት (Test Admission Ticket) መያዝ አለባችሁ 4.ስልክ ይዞ ወደ መፈተኛ አዳራሽ መምጣት ክልክል ነው 5.ከተመደቡበት የፈተና አዳራሽ ውጭ መፈተን መገኘት አይቻልም 6.መሰረታዊ የሂሳብ ስሌቶችን ብቻ የሚሰራ ካልኩሌተር መያዝ የሚቻል ሲሆን ከላይ የተዘረዘሩትን የፈተና ሕጎች በማወቅም ይሁን ያለማወቅ ተግባራዊ ያላደረገ ተፈታኝ የማናስተናግድ መሆናችንን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡ ዕውቀት ለልህቀት! ወራቤ ዩኒቨርሲቲ Source: Worabe university Facebook page Follow us @gatstudy
2