Notice❕ ለነገ የNGAT ተፈታኞች ዛሬ NGAT ፈተና ከወሰዱ ተፈታኞች ባገኘነው መረጃ መሰረት፣ ፈተናው… — GAT Exam Guide — TG.ME

#Notice

ለነገ የNGAT ተፈታኞች

ዛሬ NGAT ፈተና ከወሰዱ ተፈታኞች ባገኘነው መረጃ መሰረት፣ ፈተናው በተወሰነ መልኩ ከበድ የሚል እንደነበር እና ዋናው ፈተና የሰዓት አጠቃቀም እንደነበረ ተረድተናል።

👉 ነገ ፈተናውን የምትወስዱ ተፈታኞች የሚከተሉትን ወሳኝ ነጥቦች እንመክራለን፡

👉 አትደናገጡ፡ የዛሬዎቹ ተፈታኞች ፈተናው ከባድ ነበር ማለታቸው የናንተንም ፈተና ከባድ ያደርገዋል ማለት አይደለም። እያንዳንዱ ሰው የተለያየ ዝግጅት እና የፈተና አቀራረብ ስላለው የሰውን ወሬ ሰምታችሁ ሞራላችሁ አይውረድ።

👉 ሰዓትዎን በአግባቡ ይጠቀሙ፡
በአንድ አስቸጋሪ ጥያቄ ላይ ብዙ ጊዜ አያባክኑ። ሰዓቱን በጥብቅ ይከታተሉ።

👉 ከባድ ወይም ረጅም ጊዜ የሚወስድ ጥያቄ ሲያጋጥማችሁ ምልክት አድርጋችሁ አልፉት፤ በመጀመሪያ ቀላል የሆኑትን ጥያቄዎች በመስራት ነጥብ ሰብስቡ።

👉 ቀላል ጥያቄዎችን ሰርታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ በተረፋችሁ ጊዜ ወደ አልፋችኋቸው ጥያቄዎች ተመልሳችሁ ስሩ።

👉 ትኩረታችሁን አትበታቱ

ለነገው ፈተና ተፈታኞች በሙሉ መልካም እድል እንመኛለን!

@gat_guide
❤31👍13
August 26, 2026 5.2K 23 8