ኢትዮጵያዊቷ ሩት ይርጋለም በዓለም አቀፉ የሚስ ወርልድ 2026 የባህል ትዕይንት ከምርጥ ተወዳዳሪዎች ተመደበች
በዓለም አቀፉ የሚስ ወርልድ 2026 የቁንጅና ውድድር የሀገራት ባህላዊ ጭፈራዎች ማሳያ መድረክ ኢትዮጵያን ወክላ የተሳተፈችው ሩት ይርጋለም ከፍተኛ ብቃት ካሳዩ ተወዳዳሪዎች መካከል በዋናነት መመረጧ ታወቀ።
በውድድሩ አዘጋጆች ይፋ በተደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ግምገማ የኢትዮጵያ ተወካይ ሩት ይርጋለም በባህላዊ ውዝዋዜዋ እና በደማቅ ሀገራዊ አልባሷ የዳኞችን እና የታዳሚዎችን ቀልብ በመሳብ በምርጥ ፈጻሚዎች ዝርዝር ውስጥ ስሟ በቀዳሚነት ሊካተት ችሏል። ይህ የባህል ማሳያ መድረክ ተወዳዳሪዎች የየሀገራቸውን ጥንታዊ ቅርስ፣ ታሪክ እና ውብ እሴት ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁበት ቁልፍ የውድድሩ ምዕራፍ ነው።
በዚህ ዓለም አቀፍ የባህል ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ እንደ ቬትናም፣ ፊሊፒንስ፣ ፖርቶ ሪኮ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ቬኔዝዌላ እና ማሌዢያ ያሉ ሀገራት ተወካዮች የላቀ አፈጻጸም በማሳየት በተመራጮቹ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም የኮሎምቢያ፣ ብራዚል፣ ዴንማርክ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ዛምቢያ፣ ካምቦዲያ፣ ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ፣ ናይጄሪያ፣ ሲሪላንካ፣ ቦሊቪያ፣ ኩክ አይላንድስ እና ኔፓል ተወዳዳሪዎችም በደማቅ ባህላዊ ትዕይንታቸው ከፍ ያለ ነጥብ በማስመዝገብ በሃያ ምርጥ ብቃት ባሳዩ ሀገራት ተወካዮች ተርታ መሰለፋቸውን ከስፍራው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
Forwarded fromEthio Jobs Hub
5September 3, 2026 2.5K