የእረፍት ሰዓት ምልከታ || ፉልሀም 0-0 አርሰናል
👉 በመጀመሪያ የፉልሀምን ከ ኳስ ውጪ/ Out of possession ቅርፅ የአርሰናልን መሀል ለመሀል የመፍጠር አቅም የገደቡበትን መንገድ ማድነቅ ይገባል። ሳንደር በርግ ፣ ኬርኒ ፣ ጆሽ ኪንግ እና ኢዎቢ የፉልሀም 2ኛው መስመር የአርሰናልን የፈጠራ አቅም በደንብ ቀንሰውታል።
👉 ከማርቲኔሊ ይልቅ ትሮሳርድ ቋሚ ሆኖ መጀመሩ 2V1 ሁኔታዎች ብዙ ጊዜ ከመኖራቸው አንፃር በዚህ ረገድ ትሮሳርድ ከ wide area'ዎች ቡድኑ control እንዲኖር ለማድረግ የሚመስል ሲሆን ትክክለኛ ውሳኔም ይመስላል ለጨዋታው
👉 ኤብሪቼ ኢዜ የቀኝ #8 ቦታ ላይ ራሱን ያገኘ አይመስልም ከነፃነት አንፃር ገደቡ ላልቶለት roam እያደረገ ቢጫወት በተለይ ወደ ግራ ሲያዘነብል የተቆለፈን የተቃራኒን ቡድን መዋቅር ለመስበር አንዱ መሳሪያ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።
👉 ቪክቶር ዮኬሬሽ እና ኤዜ ከእረፍት መልስ ከዚህ የተሻለ ነገር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። የኩዌንካ እና አንደርሰን ጥምረት ብዙ የመሮጫ ስፔስ አልሰጠውም ነበር ለዮኬሬሽ አሁን ዲዮፕ መግባቱ ገና የ unit ውህደት ከመፈለጋቸው አኳያ የተሻለ ጊዜ እና ቦታ ሊያገኝ ይችላል።
👉 ራውል ሄሚኔዝ ፉልሀም ከዚህ ጨዋታ አንዳች ነገር ይዞ የሚወጣ ከሆነ ትልቁ ምክኒያት የሚሆን የሚል ግምት አለኝ።
👉 ምናልባት ሙሉ ዝግጁ ከሆነ ኤታን ንዋኔሪ ሌላ አማራጭ መሆን ይችላል ለሚኬል አርቴታው ቡድን
t.me/Footyview

2
1October 18, 2025 521 1 3