─────
ባርሴሎና እና ማንችስተር ሲቲ በተከላካዩ ኤሪክ ጋርሺያ
ዝውውር ላይ ከስምምነት መድረስ አልቻሉም።
ምክንያቱም ማንችስተር ሲቲዎች የሚፈልጉት 23 ሚሊየን
ዩሮ + 12 ሚሊየን ዩሮ ቦነስ ይፈልጋሉ። ነገር ግን
ባርሴሎናዎች ለተጨዋቹ ከ 10 ሚሊየን ዩሮ በታች
መክፈል አይፈልጉም።(telegraph)
──────────────────────────
አርሰናል ለገንዱዚ ዝውውር 40 ሚ. ፓውንድ ይፈልጋል፡፡
ፒኤስጂ አማካዩን ለማስፈረም የሚደረገውን ፉክክር
ተቀላቅሏል፡፡( Football London)
──────────────────────────
ትላንትና ከቸልሲ ጋር በይፋ የተለያየው ብራዚላዊው
አማካይ ዊልያን በአርሰናል የሶስት አመት ኮንትራት
እንደሚፈርም ይጠበቃል እንደአማራጭ አርሰናል
ለተጨማሪ 12 ወራት ለማራዘም በሚችለው ኮንትራት።
(Telegraph - subscription required)
──────────────────────────
የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ አማካይ የነበረው አንጄል
ጎሜዝ ወደ ሊል በአምስት አመት መቀላቀሉ ተረጋግጧል
ነገር ግን የተሻለ የጫወታ ልምምድ እንዲያገኝ በማሰብ
ወደ ፖርቹጋሉ ክለብ ቦቬስታ ክለብ በውሰት መላካቸውም
ተረጋግጧል። (Guardian)
──────────────────────────
ጁቬንቱስ ከዚህ ቀደም የ 28 አመቱን ጣልያናዊ አማካይ
ጆርጊኒዮን ከቸልሲ የማስፈረም እቅዱን በመተው
ፊታቸውን የሀገሩ ልጅ ወደሆነው የ 20 አመቱን አማካይ
ሳንድሮ ቶናሊን አዙረዋል።እንደሚታወቀው የተጫዋቹ እናት
ክለብ የሆነው ብሬሺያ ወደ ሴሪኤ በመጣ አመት ተመልሶ
ወደ ሴሪቢ ተመልሶ ወርዷል።(La Gazzetta dello
Sport, via Mail)
──────────────────────────
የሲቪያው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሞንቺ የ 32 አመቱን
ክሮሺያዊ አማካይ ኢቫን ራኪቲችን በዚህ ክረምት
በድጋሚ ከባርሴሎና ማስፈረም ከባድ እንደሆነ
ገልፀዋል። (Diario de Sevilla, via Evening
Standard)
──────────────────────────
የማንችስተር ዩናይትዱ አማካይ ዳይለን ሌቬቲት በቀጣዩ
ሲዝን በውሰት ሊልኩት አስበዋል፤የ 19 አመቱ ዌልሳዊ
ወደ ሻምፕዮን ሺፑ ክለቦች እንደሚያቀናም ተዘግቧል።
(Manchester Evening News)
──────────────────────────
ዛሬ እና ነገ የሚደረጉ የዮሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ
ጨዋታዎች
ዛሬ ነሀሴ 04
ኢንተር ሚላን 4:00 ሌቨርኩሰን
ማን ዩናይትድ 4:00 ኮፐንሀገን
ነገ ነሀሴ 05
ሻካታት ዶኔትስክ 4:00 ባዜል
ወልቭስ 4:00 ሴቪያ
August 10, 2020 10.8K 5