የደቡብ ኮሪያው ኬ ሊግ ከብዙ ክልከላዎች ጋር አዲሱን የውድድር ዘመን ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል....
እግር ኳስ በመላው ዓለም በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ ሰንብቶ አሁን ብቅ ማለት ጀምሯል።
በአውሮፓ የጀርመን ቡንደስሊጋ እንዲጀመር ይሁንታ አግኝቷል። በቀጣዩ ወር ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም መከናወን ይጀምራሉ
የቱርክ ሱፐር ሊግ በሰኔ ወር ወደ ውድድር ለመመለስ ተዘጋጅቷል።
በአንድ እስያዊት ሀገር ደግሞ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች መደረግ ጀምረዋል። ከቀጣዩ ወር ጀምሮ የነጥብ ጨዋታዎች መከናወን ይጀምራሉ ።
ደቡብ ኮሪያ ከቻይና በመቀጠል በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ቀዳሚዎቹ ሀገራት አንዷ ናት ።በዚህ ምክንያት በየካቲት ወር ወደ ውድድር ሊመለስ ታስቧል።
ቅዳሜ ለት ተጫዋቾች ወደ ውድድር ስፖርት በመመለስ የቤላሩስ ፣ ቡሩንዲ ፣ ታጂኪስታን እና ኒኳሯጓን ተጫዋቾቾች ይቀላቀል።
በውድድር ዘመኑ ማስጀመሪያ ጨዋታ ባለፉት ሶስት የውድድር ዘመናት አሸናፊ የነበረው ጆንቡክ ከ ሱዎን ብሉዊንግ ይጫወታል።
ውድድሩ ሲጀመር ደጋፊዎች ወደ ሜዳ እንዳይገቡ ይታገዳሉ፣ የተለየ የደህንነት እርምጃዎች ተግባራዊ ይሆናሉ።
ከእነዚህ መካከል መጨባበጥን መከልከል፣ ተጫዋቾች ከቡድን ጓደኞቻቸው - ከተቃራኒ ቡድን ተጫዋቾች --እና ጨዋታውን ከሚመሩት ዳኞች ጋር የሚያደርጉት ንግግር የተገደበ እንዲሆን ተወስኗል። አሰልጣኞች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንዲያደርጉም ይገደዳሉ።
" ተጫዋቾች ሜዳ ላይ አብዝቶ ከመትፋት አሊያም ከመናፈጥ ሊቆጠቡ ይገባል " ሲሉ የኬ ሊግ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ ዉ ቹንግ-ሲክ ተናግረዋል።
"በጨዋታ ወቅት የመትፋት እና ተጠጋግተው የማውራት ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል።"
የ ኬ ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት በ20 ጎሎች የሚመራው አውስትራሊታዊው አዳም ታጋርት እነዚህ አዲስ ደንቦች እንዴት ባለ መልኩ ሊተገበሩ እንደሚችሉ እርግጠኛ አለመሆኑን ተናግሯል።
"ሙሉ ማብራሪያው እስኪሰጠን ድረስ እየተጠባበቅን ነው" ሲል የብሉ ዊንግስ አጥቂ ከቢቢሲ ስፖርት ተናግሯል።
" ተጫዋቾች በማውራታቸው ብቻ ካርድ የሚመዘዝባቸው ከሆነ በርካታ ተጫዋቾች በቀይ ካርድ ሲሰናበቱ ልንመለከት እንችላለን " ብሏል።
May 8, 2020 9.3K 7