ሰላም እንደምን አላችሁ!
ፕሪስቴጅ አዲስ ከታዋቂው የቤዝ ጊታር ተጫዋች እና የሮሃ ባንድ መስራች አባል ጆቫኒ ሪኮ ጋር፣ በሙዚቃው ዓለም ያሳለፋቸውን የአምስት አስርት ዓመታት የስኬት ጉዞዎች የምናከብርበት ልዩ ምሽት ተዘጋጅቷል!
በዚህ አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ ጆቫኒ ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን፣ ስለአሁኑ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ዕድገት፣ እንዲሁም ስለ ህይወት እና የጥበብ ተሞክሮዎቹ ጥልቅ ትዝታዎችን ያጋራናል። በተጨማሪም ከእናንተ ከወዳጅ እና አድናቂዎቹ የሚነሱ ጥያቄዎችን ማክሰኞ ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል።
እንዳያመልጥዎ፤ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል!
ℹ️ የፕሮግራም ዝርዝር፡
📅 ቀን፡ ጳጉሜን 3፣ 2018 ዓ.ም
📍 ቦታ፡ ሳችሞ ሴንተር (Satchmo Center)፣ አሜሪካ ኤምባሲ
🕗 ሰዓት፡ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት (በኢትዮጵያ አቆጣጠር)
🔗 አሁኑኑ ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👇
https://jazzio.land/register
🤝 ከራዲያንት ፊልምስ እና ከአዲስ አበባ አሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር የቀረበ።
#BeyondTheScreen #PrestigeAddis #GiovanniRico #RohaBand #EthiopianMusic
@prestigeaddis










