ማውገዝና ገዳም መግባት የሲኖዶስ ሥራ ሕንጻ ማነጽ፣ መኪና መግዛት ደሞዝ መጨመር፣ ጳጳስ ማዘዋወር አይደለም።… — ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን) — TG.ME

ማውገዝና ገዳም መግባት 

የሲኖዶስ ሥራ ሕንጻ ማነጽ፣ መኪና መግዛት ደሞዝ መጨመር፣ ጳጳስ ማዘዋወር አይደለም። ኹለንተናዊ የካህናትና የማእመናንን ደኽንንነት መጠበቅ ከሚያጠቃቸውም መከላከል ነው። ሲኖዶስ ያስፈለገው ለቤተክርስቲያን ችግር የኾነን ጉዳይ መፍትሔ መስጠት ነው። 

ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ተልእኮ እንጂ የደሞዝ ማስተካከያ ቅያሬ ማስፈጸሙያ የቦዝነስና አስተዳደር ጽ/ቤት አይደለም። የሕንጻ ቤተክርስቲያን መገንባት በቁጥር መብዛት የምእመናንን መብዛት የቤተክርስቲያንን ማደግ አያሳይም። 

ከቅዱስ እስጢፋኖ ሞት እስከ ታላቁ ቆስጠንጢኖስ ድረስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን አልተገነባም። ክርስቲያኖች በዋሻ በዛፍ ስር በየቋጥኙ በየግለሰብ ቤት ተደብቀው ነው ይኖሩ የነበሩት። ነገር ግን የሚያምኑ ክርስቲያኖች ቁጥር ይጨምር ዋሻዎቹ እየሞሉ በየከተማው ዐዳዲስ የአማንያን መሰብሰቦያ ይፈጠሩ ነበር። 
ከበሮ መደለቅ ማህሌት መቆም ሕንጻ ማነጽ ሰበካ ጉባኤ ማደራጀት አልነበረም። ዋና ሥራቸው ክርስቲያኑን በወንጌል ማጽናት ያላመነውን ማስመን ያመነውን አስተምሮ ማጥመቅ ማቁረብ ሕይወቱን ከዓለም ለይቶ ራሱን ለሰማዕትነት እንዲያዘጋጅ ማብቃት ነው። ይኽ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በስፋት የመዘገበው እውነታ ነው። 

 የቀደመችውን ቤተክርስቲያን ስናስብ ቤተክርስቲያን የመሩ ሊቃነ ጳጳሳት ስናይ ከዛሬዋ ቤተክርስቲያን ጋር ስናስተያይ ዓለማዊነት የበላት ቤተክርስቲያን ኾናለች። የጥንቱ አማኝ ከዓለም ወደ ቤተክርስቲያን ይመጣ ነበር። ዛሬ ካህናቱም ምእመኑም ቤተክርስቲያንን ዓለም አድርጓታል።

ሲኖዶሱ ይኽንን አማኙን የሚጨርሰውን አስቦ አቅዶ የሚያጠፋውን መንግሥት መግደል ማፍረስ አቁም ብሎ ማሳሰብ ማስጠንቀቅ ከዚያም ማውገዝና ምእመናን ሃገራችሁን ቤተክርስቲያንን በያላችሁበት ጠብቁ ብሎ በየሃገረ ስብከቱ ወደ አገልግሎት መግባት ነበረበት። 

እነርሱ ከመንግሥት ጋር ተግባብቶ መሥራት ያስፈልጋል እያሉ ሃገር አልባ ቤተክርስቲያን አልባ እያደረጉን ነው። በየአጥቦያው ካህናቱ ጉዳዩን ከምእመኖቻቸው ጋር አንሥተው አይመክሩም። በየዱር ለሚወድቁት ምንም ማድረግ አይፈልጉም። ካህናቱ የየአጥቢያው ወር ኀዊ ገቢ ነው የሚያሳስባቸው። ሞርጌጅ ፣ ዐዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ነው ዋና አጀንዳቸው። 

አብይን ያወገዙ አቡነ ሉቃስ ዛሬ የሚሄዱበት ቤተክርስቲያን አጥተው ቤታቸው ተቀምጠዋል። ቤተክርስቲያን እንዳይደርሱ ያደረጋቸው ደግሞ ሊቀ ጳጳሱ ፣ ካህናቱ ምእመናኑ ናቸው። በየደረጃቸው።

ምእመኑንም ለምን ብሎ አይጠይቅም፣ ካህኑም እንዴት ብሎ አያሳስብም። ተያይዞ ማለቅ ማለት ይኽ ነው። ማሰብ ያልጀመረ ሕዝብ አያሸንፍም። 

ንዋይ ካሳሁን
👍15❤1🤔1
August 28, 2026 3.4K 4 9