ነፍሴ ሆይ!!
ታላቁ አባ መቃርስ ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን መልእክት ነው። (መጽሐፈ ገነት 168ኛ ትምህርት)
ቀናችን ሳይጨልምና አንደበታችን እና እጃችን ሳይታሰር ነፍሳችን ከሥጋችን ሳትወጣ ፍርሃትና ድንጋጤ መንቀጥቀጥና ልቅሶ ባለበት የፍርድ አደባባይ በኃጢአት አንገታችንን ደፍተን ክፉ ሥራችን እንሸከማለንና ክፉ ሥራችንን እንተው።
እኔ አባ መቃርስ ከሰማሁት ነገር የተነሣ አብዝቼ መራራ ለቅሶን አለቀስኩ። ችግረኛን ካልወደድንና ያለንን ሁሉ ካልሰጠን ሐሳባችን ሁሉ ወደ ሰማይ አንድነት እንዲሆን በማገልገል በልመና በኀዘንና በለቅሶ ጥቅማችንንና ፍላጎታችንን እንተው።
አስቸጋሪ ነፍስ ሆይ እስከ መቼ ድረስ ከመድኅኒትሽ ትሰንፊያለሽ ወደ ፈጣሪሽ እግዚአብሔር አትመለሺምን። ዝሙትን የማትጠግቢ እስከ መቼ ነው።
እነዚኽን መስረቅና መበደልን፣ ትዕቢትና ቅንዓት ገንዘብን መሰብሰብን ክፋትንና መንጠቅን ያለ ልክ መጥገብን መግደልን ነገር መስማትን ከንቱ ትዕቢትን የአምላክሽ የእግዚአብሔርን ስም እየጠራሽ በሐሰት መማልን፣ መቀመጥን ቁጣን ከጣት እስከ ማታ ብስጭትን በቀንና በሌሊት መርከስን ችግረኞችን መሳደብና መጥላት የማትጠግቢው እስከ መቼ ነው። አንቺ አስቸጋሪ ነፍስ ያለበደልና ያለ ኃጢአት የምታበሪ ንጹሕ አድርጎ የፈጠረሽ እግዚአብሔር አይደለምን።
ንዋይ ካሳሁን
12
9August 27, 2026 1.3K 11