ሥራ ቦታ ለምን እንሄዳለን?
ሥራ የምንሄደው ገንዘብ ለማግኘት ከዚያም ለኑሮ የሚኾነን ገንዘብ ለማግኘት ነው? እግዚአብሔር ሥራን የሰጠን ገንዘብ እንድናገኝ ነው? የምንማረው ለገንዘብ ነው? ሥራ ለማግኘት መማር ተምረን ሥራ ማግኘነት፣ ሥራ ይዘን ገንዘብ ማግኘት ገንዘብ አግኝተን ኑሮን ለመኖር።? እንስሳት ምግብ ለማግኘት ሰው የሚያደርገውን አያደርጉም ወደ አንዱ ስፍራ ይሄዳሉ ምግባቸው ይሰጣቸዋል። ታድያ ሰው ሥራ የሚሄደው ለምንድነው? “ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፥ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?” ማቴ.6:26
እግዚአብሔር ወደ ሥራ እንድንሄድ የሚያደርገው ሰዎች ጋር እንድንገናኝና ለሰዎች መልካምነትን በማሳየት በነርሱ ላይ በጎ ተጽዕኖ ለማሳደር ሲኾን መልካምነት በማጋራት የተመቸ የሥራ ቦታ መፍጠር ነው። “እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል? ወደ ውጭ ተጥሎ በሰው ከመረገጥ በቀር ወደ ፊት ለምንም አይጠቅምም።” ማቴ.5:13
አንዱ ለአንዱ መልካም ነገር ለመሥራትና ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር ነው። ምክንያቱም የሥራ ስፍራ ውድድር፣ ፋክክር፣ ምቀኝነት፣ ክፋት የሞላበት ስፍራ ነው። በዚኽም ምክንያት አንተ ለሰዎች ሰዎች ለአንተ ጠቃሚ ነገር እንዲያደርጉ ነው ስለዚኽ ዓለምን ኹል ቀን መልካም እንድናደርግ ነው።
ከሥራ በኋላ ወደ ቤት የሚመለስ ሰው ብዙ ምስቅልቅል ካለበት የሥራ አካባቢ በመኾኑ ወደ ወደቧ የምትሄድን መርከብ እንመስላለን። እግዚአብሔር የምንመገበውን ቀጥታ አይሰጠንም፣ በትምህርት፣ በሥራ በኩል ነው።
ንዋይ ካሳሀን
Forwarded fromፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)

21
1
1August 27, 2026 1.1K 1 6