ድሃ ሆኖ ሥራን መናቅ የድብቁው የአዕምሮ ክፍል ውቅር Unconscious mind setup ድሃ ሆኖ ሥራን… — ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን) — TG.ME

ድሃ ሆኖ ሥራን መናቅ 

የድብቁው የአዕምሮ ክፍል  ውቅር Unconscious mind  setup

ድሃ ሆኖ ሥራን መናቅ በብዙ ታዳካሳሁንበረሰቦች ውስጥ የሚታይ፣ ለቀጣይ ድህነት እና ለሀገር ኋላቀርነት ዋና ምክንያት የሆነ ሥነ ልቦናዊና ባህላዊ እንቆቅልሽ  (Social Paradox) ነው። 

​1. የችግሩ ዋና ሥነ ልቦናዊ ምክንያቶች

የተሳሳተ የክብር ብያኔ (False Pride / Ego Defense)፦ አንድ ሰው በድህነት ውስጥ እያለ የጉልበት ወይም ተራ የሚባል ሥራ ሲንቅ፣ የራሱን ዝቅተኛነት ወይም ድህነት የመሸፈኛ ሥነ-ልቦናዊ መከላከያ (Defense Mechanism) ማድረጉ ነው። "እኔ እኮ የዚህ አይነት ሰው አይደለሁም" የሚለው የተሳሳተ የበላይነት ስሜት (Ego) እውነታውን እንዳይቀበል ያደርገዋል።

የሕዝብ አስተያየት ፍርሃት (Fear of Social Stigma)፦ "ሰው ምን ይለኛል?" የሚለው ጭንቀት ከድህነት መውጫው በር ላይ ትልቅ እንቅፋት ይሆናል። ከረሃብ እና ከእጅ ወደ አፍ ህይወት ይልቅ የሰዎች አሉታዊ አስተያየት ይበልጥ የሚያስፈራቸው ሰዎች ሥራን ይመርጣሉ።

የሥራ ክብር ባህል አለመለመድ (Lack of Dignity of Labor)፦ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሥራን በደረጃ የማስቀመጥ (Occupational Hierarchy) ባህል አለ። ቢሮ መቀመጥ እንደ ክብር፣ ንግድ ወይም የጉልበት ሥራ ደግሞ እንደ ውርደት የመታየት አመለካከት ሕሊና ላይ ስለሚቀርፅ ነው።

​2. የሚያስከትለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት

የተዛባ ጥገኝነት (Parasitic Dependency)፦ ሥራ የሚንቅ ድሃ በራሱ ሰርቶ ከመኖር ይልቅ በቤተሰብ፣ በዘመድ ወይም በማኅበረሰብ እጅ ላይ ጥገኛ መሆንን ይመርጣል። ይህ ደግሞ በራስ መተማመኑን ያጠፋዋል።

የወንጀል እና የሱስ ተጋላጭነት፦ ሕጋዊ እና ጥረት የሚጠይቅ ሥራን የሚንቅ ሰው በቀላሉ ወደ አቋራጭ መንገዶች (ማጭበርበር፣ ስርቆት) ወይም ወደ ተስፋ መቁረጥና ሱስ ውስጥ የመግባት እድሉ ከፍተኛ ነው።

የድህነት ዑደት መደጋገም (Cycle of Poverty)፦ ዛሬ የሚናቁትን ትንንሽ ስራዎች አለመስራት ነገ የሚመጡ ትልልቅ እድሎችን ይዘጋል። ጅምር የሌለው ህይወት ደግሞ ድህነትን ለቀጣይ ትውልድ ያስተላልፋል።

​3. በአመለካከት ላይ ሊደረግ የሚገባው ለውጥ
"ሥራ ክብር ነው፤ የሚያዋርደው ድህነትና ልመና እንጂ ሕጋዊ ሥራ አይደለም።"
ከትልቅ ሕልም ጋር ትንሽ መጀመር፦ የትኛውም ትልቅ ነጋዴ ወይም ስኬታማ ሰው የጀመረው ከተራ እና አነስተኛ ሥራዎች ነው። ሥራን አለመናቅ ማለት የስኬት የመጀመሪያው ደረጃ ነው። መሥራትን ያልወደደ ሰው እድሜ ልኩን ሎተሪ እንዲደርሰው ሲመኝ ይኖራል። 

የአእምሮ ነፃነት፦ የሰዎችን አስተያየት ፈርቶ ከመቀመጥ ይልቅ፣ በገዛ ላብ የሚገኝ ሳንቲም የሚያስገኘውን ነፃነት እና የህሊና እረፍት ማስቀደም።

የሥራ እሴትን ማደስ፦ ማኅበረሰቡም ቢሆን የትኛውንም አይነት ሕጋዊ ሥራ የሚሰሩ ሰዎችን የማክበር እና የመደገፍ ባሕል ማዳበር አለበት።

ኢትዮጵያውያን ሸክላ የሚሠሩትን ሸክላ ሠሪ ሸማኔውን ቁጢጥ በጣሽ፣ አራሹን አፈር ገፊ አንጥረኛውን ብረት ቀጥቃጭ፣ ነጋዴውን መጫኛ ነካሽ፣ ባለ መድኃኒቱን ሥር ማሽ ቅጠል በጣሽ እያለ ሥራ ሲያናንቅ የኖረ ማኅበረሰባዊ ደመ ነፍስ collective unconscious ያለው ሕዝብ ነው። 

ንዋይ ካሳሁን
❤17👍3
August 27, 2026 1K 6