ፍኖተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት: post #2799 — TG.ME

#እንኳን_ለጾመ_ፍልሰቷ_በሰላም_አደረሳችሁ
ፍልሰታ ማለት ፈለሰ፤ ተሰደደ፤ ተጓዘ፤ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ «ፈለሰት ማርያም እምዘይበሊ ኀበኢይበሊ፤ ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች» በመባል የሚታወቀውና ከእመቤታችን የዕረፍትና የዕርገት ታሪክ ጋር የተያያዘው ጾመ ፍልሰታ፣ ከነሐሴ ፩ እስከ ፲፭ ቀን ድረስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች በኅብረት የሚጾም ታላቅ ጾም ነው።

እመቤታችን በምድር ፬፻፵፱ ዓ.ም ጥር ፳፩ ቀን ካረፈች በኋላ፣ ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መካነ መቃብር ሲሔዱ አይሁድ በምቀኝነት ተነሥተው ሊቃጠሉትና ሊወስዱት ፈለጉ። በዚህ ጊዜ ታውፋንያ የተባለ አይሁዳዊ የአልጋውን ሸንኮር በእጁ ሲይዝ የእግዚአብሔር መልአክ እጁን በሰይፍ ቆረጠው፤ ነገር ግን የምሕረት እናት በሆነችው በእመቤታችን ምሕረትና በቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎት እጁ ዳነለት።

ከዚህ በኋላ የእመቤታችን ክቡር ሥጋ በመላእክትና በዮሐንስ ወንጌላዊ አማካኝነት ወደ ኤደን ገነት ከተወሰደ በኋላ፣ ሐዋርያት ነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ በጾምና በጸሎት በመጽናታቸው በ፲፬ኛው ቀን ሥጋዋ ተሰጥቷቸው በጌቴሴማኒ በክብር ቀብረዋታል። እመቤታችንም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ሞትን ድል አድርጋ ተነሥታለች፤ መላእክትም እየዘመሩላት ወደ ሰማይ ስታርግ ከሕንድ ሀገር ስብከቱ ይመለስ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ተመልክቶ ሰበኗን ተቀብሏል።

ቅዱስ ቶማስ ለሐዋርያት ሲነግራቸው መጀመሪያ ላይ ባያምኑም መቃብሩን ከፍተው ሲያዩት ባዶ ሆኖ አገኙት፤ ቶማስም ሰበኗን አሳይቷቸዋል። ሐዋርያትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በዓይን ለማየት እንደገና ነሐሴ ፩ ቀን ሱባኤ ጀምረው በ፲፮ኛው ቀን የጌታን መገለጥና በረከት አግኝተዋል። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ክርስቲያኖች ሁሉ ይህንን የሱባኤ ወቅት በጾምና በጸሎት እያከበሩ ከእመቤታችን በረከት ይካፈላሉ።
✝️ አቃቂ ፋንታ ደብረ ፅጌ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት ✝️
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
የቴሌግራም_ገፃችን
https://t.me/finote_Tsidiki_0613
ዩቱዩብ_ገፃችን
https://youtube.com/@finotetsedik?si=OGHqCSjzAlH-pGxf
የፌስቡክ_ገፃችን
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082976035006
የቲክቶክ_ገፃችን
https://www.tiktok.com/@finote13?_r=1&_t=ZS-93b2aRbXvY0
የኢሜል_አድራሻችን
[email protected]
መልእክት_ለመላክ
@finote_Tsidiki13bot
​#ፍኖተ_ጽድቅ #ሰንበት_ትምህርት_ቤት
Telegram
ፍኖተ ጽድቅ ሰንበት ትምህርት ቤት
ይህ የፍኖተ_ፅድቅ ሰ/ት/ቤት ትክክለኛው የቴሌግራም ገፅ ነው። 🛑ሊንኮቹን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ🛑 ✨✨✨✨✨✨✨ ▭▭▭ ◎⃝ ◎⃝ ⃟ ◎⃝ ◎⃝ ▭▭▭ 🔎ፌስቡክ ገፅ https://www.facebook.com/profile.php?id=100082976035006 🔎 ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@finote_tsidik_s.t 🔎ቴሌግራም ገፅ፦
🙏2
August 7, 2026 343 1