የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ ውጤታማ ሥራ እያከናወነ መሁኑን አሥታወቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም
የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ ውጤታማ የሥራ አፈፃፀም ላላቸው ባለድርሻ አካላት ዕውቅና ሰጥቷል። በዚህ የምስጋና እና የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የመከላከያ የሠው ሀብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል አጫሉ ሸለመ ተገኝተዋል።
በሥራ አፈፃፀማቸው ከፍተኛ ብልጫ ያመጡ የክልል እና የዞን ላይዘን ጽህፈት ቤቶች፣ በስራቸው የሚገኙ ዞን ላይዘን ፅህፈት ቤቶችን በማስተባበር ያለሰለሰ ጥረት አድርገው ቢሮው ግብ ላይ እንዲደርስ ላደረጉ አመራሮችና አባላት ነው ዕውቅና የተሰጠው።
ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመ ዕውቅናና ሽልማት አባላቶች የበለጠ ኃላፊነት ተሰምቷቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ በታማኝነትና በታታሪነት እንዲሰሩ የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመው ቀጣይ የሚሰጡ ግዳጆችንና ተልዕኮዎችን በአስተማማኝ ደረጃ ለመወጣት ዕውቅና የሚያነቃቃ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ ሜጄር ጄነራል ጀማል መሐመድ
በበኩላቸው የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ቢሮ በአዋጅ ቁጥር 327/1995 ከተቋቋመበት ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ የብሔራዊ ተጠባባቂ ኃይል ከሁሉም ክልሎች እየመለመለ ፣ እያሰለጠነ፣ እያደራጀና ወደ ግዳጅ እያሰማራ መቆየቱን አብራርተዋል፡፡
ቢሮው በተቋሙ የተሰጠው የሠራዊት ምልመላ ስራዎች የካሳ ክፍያ ስራዎች፣ የዘላቂ ጡረታ መብት የማስከበር ስራዎች፣ የሰራዊት ግንባታ ስራዎች እና በርከት ያሉ ሌሎች ተልዕኮዎች በመቀበል ከመከላከያ ሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ እና ከመከላከያ ፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ ጋር በመሆን ክልል እና ዞን ላይዘን ጽህፈት ቤቶች ጋር በመቀናጀት ሥራዎች መስራቱንና ውጤታማ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ መረጃውን ያደረሰን የማሥተባበሪያ ቢሮው ፅህፈት ቤት ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
44
10
1October 8, 2026 5.4K 2