ለመከላከያ መቻል እጅ ኳስ ቡድን አሸኛኘት ተደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 22 ቀን 2019… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ለመከላከያ መቻል እጅ ኳስ ቡድን አሸኛኘት ተደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም

በአንጎላ ሉዋንዳ በሚካሄደው 47ኛው የአፍሪካ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የመከላከያ መቻል እጅ ኳስ ቡድን በዛሬው እለት በክለቡ መኖሪያ ካምፕ የክለቡ ስራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን እና ኮሎኔል ከፍያለሁ ረጋሳ የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ አባል በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል።

የራሳችሁን ታሪክ ለመፃፍ መዘጋጀት አለባችሁ ያሉት የመከላከያ መቻል ስፖርት ክለብ ስራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን ሠራዊታችን በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎች ውጤት እያስመዘገበ እንዳለው ሁሉ እናንተም በምትሄዱበት ውድድር ላይ አሸናፊ በመሆን ሀገራችሁንና ተቋማችሁን ማስጠራት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።

ብርጋዲየር ጄኔራል ኑሩ ስፖርተኞች የሀገራቸውን ስም በጥሩ ስፖርታዊ ዲሲፕሊን ማስጠራት እንዳለባቸው አንስተው የምታገኙት ተሞክሮና ልምድ የበለጠ ስኬት የምታስመዘግቡበት መሆን አለበት ሲሉ አመላክተዋል።

የመከላከያ መቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ አባል ኮሎኔል ከፍያለሁ ረጋሳ የስራ አመራር ቦርዱ ሁሌም ከስፖርተኛው ጋር መሆኑን ጠቁመው የመቻል ስፖርተኞች የሀገራቸውንና የተቋማቸውን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

በሽኝት ፕሮግራም ላይ የክብር እንግዶቹ ለቡድኑ አሰልጣኝና አምበል ሰንደቅ ዓላማ አሥረክበዋል። ቡድኑ አባላት ይዞ በነገው እለት ወደ ውድድር ስፍራው አንጎላ ሉዋንዳ ጉዞውን ያደርጋል።

ዘጋቢ ቃልኪዳን በላቸው
ፎቶግራፍ ሌሊሴ ዮሃንስ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤33🙏14👍13🔥3
October 2, 2026 7.4K