በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ የተሰማራው ሠራዊት በፅንፈኛው ቡድን ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሷል። የኢፌዴሪ… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ የተሰማራው ሠራዊት በፅንፈኛው ቡድን ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም

በምሰራቅ ዕዝ የአንድ ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ምስራቅ መንበረ የክፍለጦሩ ሬጅመንቱ በደቡብ ጎንደር ዞን ፣እሰቴ ወረዳ ልዩ ስሙ ሳና ሚካኤል በተባለ አካባቢ ባደረገው ፀረ ሸምቅ ዘመቻ የህወሃትን እና የውጪ ሃይል ተልዕኮን ተቀብሎ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሰ በነበረው ፅንፈኛ ቡድን ላይ እርምጃ በመውሰድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል።

የፅንፈኛ ቡድኑን ሙትና ቁሰለኛ በማድረግ ብሬን፣ ክላሸ፣ የእጅ ቦምብ፣ የመገናኛ ሬድዮ ፣እና ሌሎች ትጥቆችን መማረኩን የገለፁት አዛዡ ከተደመሰሱት ፅንፈኞች መካከል በነሱ አሰያየም የተወርዋሪ ክፍለ ጦር ብርጌድ አዛዥ ሻለቃ ብርሃኑ ሻምበል እንደሚገኝበት ገልፀዋል።

የሬጅሜንቱ አዛዥ ሻምበል አብርሃም ቻይና በበኩላቸው በተሰጣቸው ግዳጅ መሠረት የጠላትን እንቅሰቃሴ በማጥናትና ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት ጠላትን ሙት እና ቁሰለኛ ማድረግ እንደተቻለ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የምስራቅ ዕዝ ሬጅመንቶች በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ በአብሰኪን ቀበሌ የሰላም ጥሪ ባልተቀበለው የፅንፈኛ ቡድን ላይ እርምጃ ወስደዋል።

የሬጅመንት አዛዥ ሻምበል ዳዊት አራርሳ እንደገለፁት ማህበረሰቡን ሲዘርፍ ሲገድልና ሲያሰቃይ በነበረው ፅንፈኛዉ ቡድን ላይ በተወሰደው እርምጃ አብዛኛው ሃይል ሙትና ቁስለኛ ሲሆን ፣ቀሪዉ እየተበታተነ ይገኛል።

ከህዝብ የተዘረፈ 170 ኩንታል በቆሎ፣ስንዴና ገብስ እንዲሁም ለአርሶአደሩ ይደርስ የነበረ 70 ቀረጢት የአፈር ማዳበርያ ከዘራፊዉ በመያዝ በክንደ ብርቱ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ዉሏል። ዘገባው የሥስራቅ ዕዝ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤39👍22👏19😁3🔥1
October 2, 2026 6.9K 10