በ10ኛ ዕዝ አባይ ኮር የግዳጅ ቀጠና የፅንፈኛው ታጣቂዎች እጅ ሰጡ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም
በሰሜን ጎንደር ዞን አዲአርቃይ ወረዳ ዙሪያ በፀረ-ሰላም ተግባር ተሰማርተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 15 የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች የተደረገላቸውን የሠላም ጥሪ ተቀብለው እጅ መስጠታቸውን የአባይ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ሃሺም ኢብራሂም ገልፀዋል።
ጀኔራል መኮንኑ በአካባቢው በተሰራው ጠንካራ የማግባባት ስራ በርካታ የፅንፈኛው ታጣቂዎች የተደረገላቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መግባታቸውን አውስተው ሠራዊታችን በሰራው ጠንካራ ስራ በአካባቢው የነበረውን ስጋት ማስወገድ ተችሏል ብለዋል።
የሰላም አመራጩን ተቀብለው በሠላም የገቡ ታጣቂዎች በበኩላቸው በተሳሳተ መንገድ ሀገራችንን እና ህዝባችንን በድለናል፤ አሁን ግን ከህዝባችን ጋር ሆነን ከኛ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
42
29
2September 24, 2026 4.8K 5