ጋሽ #ልደቱ ሆይ እኔ የታጠቁ ሀይሎችን ጥምረት የምቃወም መሆኑን ከየት አመጡት ? ልክ እንደ ወዳጄ ልደቱ የተሳሳተ ግንዛቤ ለያዛችሁ ግልጽ እንዲሆን እኔ የተባለውን ጥምረት አልደግፍም አለቃወምም! የማልደግፍበት ምክንያት፡ ደጋግሜ እንደምናገረው እኔ የኢትዮጲያ ውስብስብ ቀውስ በጦርነት ይፈታል የሚል ተስፋ የለኝም። በተለይ አከባቢው ላይ የተፎካካሪ ሀገራት መፋተጊያ በሆነበት በዚህ ወቅት በተጨማሪ ጦርነት ወደ ሰላምና ዲሞክራሲ የሚያሻግር ለውጥ ለማምጣት ያለው እድል እጅግ ጠባብ ነው። እድላችን እንሞክር ከተባለ እንኳን፣ የሚፈጠረው ትብብር ተለቅ ያለ ስምምነት ላይ ካልተመሰረተ፣ አገዛዙን ለመገርሰስም ሆነ ከዚያ በኋላ ሀገር ለማረጋጋት የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር አስቸጋሪ ያደርገዋል። ሰሞኑን በወልቃይትና እና ወለጋ ጉዳዮች የተነሳው አቧራም ለዚህ ስጋቴ ትክለኛነት ማስረጃ ነው። በነዚህና ሌሎች ጉዳዮች በሰል ያለና አስተማማኝ ስምምነት ላይ የተደረሰ አይመስለኝምና ይታሰብበት ማለቴን በቅን ከመቀበል ይልቅ እንደተቃውሞ መውሰድ ተገቢ አይመስለኝም። የማልቃወምበት ምክንያት፡ ምንም እንኳን በትጥቅ ትግል ሰላምና ዲሞክራሲ ማስፈን እንደማይቻል ባምንም፣ አገዛዙ የፖለቲካ ምህዳሩና ጠርቅሞና ግጭቶችን በሰላማዊ ድርድር ለመፍታት ያለውን እድል አጨልሞ ባለበት ሁኔታ፤ የተገፉ ወገኖች ነፍጥ አንግበው ማመጻቸውን ለመኮነን የሚያስችል ሞራል የለኝም። በተጨማሪም አሁን በደረስንበት ደረጃ፣ አማጺ ቡድኖች የፖለቲካችን ተጨባጭ ተዋናይ ( real, active and influential political actors) ስለሆኑ እነሱን በማግለልና በመቃወም ወደ ሰላም፣ ዲሞክራሲና ልማት መሸጋገር አይቻልም። ስለሆነም እንደኔ በሰላማዊ ትግል የምናምን ሰዎች ከመንግስትም ሆነ ከአማጺ ወገን የታጠቁ ሀይሎች በሰላማዊ ህዝብ ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ከተቻለም ልዩነቶችን በድርድር እንዲፈቱ ማነጋገር፣ ማወያየት፣ መምከር እና መገሰጽ መሞከር ይጠበቅብናል። ከዛ አልፈን ግን አማጺያን መርገም ሆነ ጦርነት እንዲፋፋም ማማሟቅ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያይላል። እኔ የምቃወመው፡ ማንኛውም የመንግስትም ሆነ የአማጺ ሀይል በየትኛውም አካባቢ በሚኖር ሲቪል ህዝብ ላይ የሚደርጉትን ግድያና ዘረፋ፣ ወጣቶችን በግዴታ ለጦርነት ማፈስ አጥብቄ እቃወመዋለሁ። ባለኝ ተሰሚነት በሚዲያም ሆነ በዲፕሎማሲው ማህበረሰብ በኩል አጋልጣለሁ። ~ ጀዋር መሀመድ ✍ ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 📌 t.me/Fastsinfo99 🌴 🌴 🌴
Telegram𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬✅|| 𝐘𝐀𝐀𝐃𝐀 ykn komii yoo qabaattan nuuf barreessaa. ✅|| ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካለዎት ይፃፉልን ✅|| write to us if you have any comments or complaints. 👀 @Fastmereja_Bot 👀ጋሽ #ልደቱ ሆይ እኔ የታጠቁ ሀይሎችን ጥምረት የምቃወም መሆኑን ከየት አመጡት ? ልክ እንደ ወዳጄ ልደቱ… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME
September 2, 2026 754 1