" ፍጥረት አይለም ሊያደርገው ሊያስበው እንኳን የማይችለው ግብ " በማለት ጣሊያናዊው የስፖርት ጋዜጠኛ እና የእግር ኳስ ተንታኙ ጋብርኤል ማርኮቲ ግቧን ይገልፃታል... የስኮትላንዱ ሀምፕደን ፓርክ (ሬንጀርስ) የእንግሊዙን ማንችስተር ዩናይትድ በ Away_Goal ያሸነፈውን የጀርመኑን ባየር_ሊቨርኩሰንን እና የ ምንግዜም ተቀናቃኙን ባርሴሎናን በአሳማኝ ሁኔታ አሸነፎ የመጣውን ሪያል_ማድሪድን ለፍፃሜ ጨዋታ አፋጧል ገና ጨዋታው በተጀመረ በ8 ኛው ደቂቃ ስፔናዊው ጉል አዳኝ ራውል_ጎንዛሌዝ ከግራ ክንፍ ከ ሮቤርቶ ካርሎስ የተሰነጠቀለትን ኳስ በቀላሉ ወደ ጎል ቀየራት ➬ ማድሪድ 1-0 ሊቨርኩሰን ጨዋታው ቀጥሏል በ 13ኛው ደቂቃ በክንፍ በኩል ፈረንሳዊው ክላውድ_ማኬሌሌ ሚሸል_ባላክን በመጥለፉ ለባየር ሊቨርኩሰን የተሰጠውን ቅጣት ምት በርናንድ ሽናይደር ወደ ግብ ሲያሻማው ብራዚላዊው ሉሲዮ በግንባሩ በመግጨት ግብ አስቆጥሮ ክለቡን አቻ አደረገ ጨዋታው እየተጋጋለ ነው ሊቨርኩሰን በ #ብራዲች #ዚኮቪች እና ባላክ ተደጋጋሚ የጎል ሙከራዎችን አደረጉ 45ኛው_ደቂቃ ከመሀል ሜዳ አካባቢ ሳንቲያጎ_ሶላሪ በግራ ክፍን በኩል ለነበረው ሮቤርቶ_ካርሎስ ኳሳን አቀበለ ካርሎስም የተሰጠውን ኳስ ወደ 16ከ 50 አሻገረው በዚህ ቅፅበት ፈረንሳዊው ታዕምረኛ #ዚነዲን_ያዚድ_ዚዳን የተሻገረውን ኳስ ማንም ባላሰበው እና ባልጠበቀው መልኩ በግራ እግሩ ቮሊ በመምታት በ ጆርጌ_በት መረብ ላይ አሳረፈው... ሪያል ማድሪድም ለ 9 ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ ጣሊያናዊው የእግር ኳስ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ #ገብርዔል_ማርኮቲ ጎሏን "ፍጥረት አይደለም ሊያደርገው ሊያስበው እንኳን የማይችል ጎል" በሚል ቃል ገልፇታል እኔ ባንተ ምክንያት በእግር ኳስ ፍቅር እብድ እንድሆን ዘንድ እንኳን ተወለድክ
ፍጥረት አይለም ሊያደርገው ሊያስበው እንኳን የማይችለው ግብ " በማለት ጣሊያናዊው የስፖርት ጋዜጠኛ እና… — ሜዳ ስፓርት በኢትዮጵያ ™ — TG.ME
June 23, 2024 712 1