#የ12ኛ_ክፍል_ብሔራዊ_ፈተና_ውጤት 2018/2026 💥 የፈተናው ውጤት መች ይፋ ይደረጋል? ውጤት ሰኞ ወይም ማክሰኞ ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል። 🌀 ውጤቱ ምን ይመስላል? በአጠቃላይ 550,210 ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ አምጥተው ማለፍ የቻሉት 12.8 በመቶ (70,544 ተማሪዎች) ናቸው። 🔹 ተፈጥሮ ሳይንስ፡ 16.5% አልፈዋል 🔹 ማህበራዊ ሳይንስ፡ 8.33% አልፈዋል 🌀 ከፍተኛ ተማሪዎችን ያሳለፉ ክልሎች/ከተማ አስተዳደሮች በቅደም ተከተል፦ 1. አዲስ አበባ (32.4%) 2. ሐረሪ (22.76%) 3. አማራ (15.0%) 4. ድሬደዋ (11.92%) 5. ትግራይ (11.2%) 💥 ከፍተኛ ውጤት ስንት ተመዘገበ? በተፈጥሮ ሳይንስ፦ 591.6 / 600 (ወንድ) - ከኦዳ ስፔሻል ቦርዲንግ - አዳማ 583 / 600 (ሴት) - ከእንጅባራ አገው ምድር ት/ቤት በማህበራዊ ሳይንስ፦ * 576.25 / 600 (ወንድ) ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት * 569 / 600 (ሴት) ከቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት 🔹 የትምህርት ቤቶች ሁኔታ፦ 100% ያሳለፉ ት/ቤቶች፦ 88 ትምህርት ቤቶች (ከነዚህም ውስጥ 37 በኦሮሚያ እና 24 በአዲስ አበባ ይገኛሉ) ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ት/ቤቶች፦ 585 ትምህርት ቤቶች 🔹 በኦንላይን እና በወረቀት ከተፈተኑት፦ በኦንላይን ከተፈተኑት፦ 18.37% አልፈዋል በወረቀት ከተፈተኑት፦ 4.2% አልፈዋል 🔹 ስለ ሬመዲያል (Remedial) ፕሮግራም፦ በዘንድሮው የሬመዲያል ፕሮግራም የሚወሰደው የተማሪዎች ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን የመቁረጫ ነጥቡ ወደፊት ይፋ የሚደረግ ይሆናል። 𝑬𝑻- 𝑴𝒂𝒕𝒉𝒔 𝑵𝒆𝒕𝒘𝒐𝒓𝒌
𝑬𝑻- 𝑴𝒂𝒕𝒉𝒔 𝑵𝒆𝒕𝒘𝒐𝒓𝒌: post #3699 — TG.ME
August 22, 2026 7.1K 4 57