ታምራት ቶላ የቤጂንግ ማራቶን ክብረወሰን ሰብሮ ሲያሸንፍ አንቺንአሉ ደሴም ድሏን ደግማለች
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ- የኢትዮጵያ አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ያላቸውን ድል አድራጊነት እና ልዩ አቅም በድጋሚ ባሰመሰከሩበት የ2026 የቤጂንግ ማራቶን ውድድር፤ የፓሪስ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ በበላይነት አጠናቋል።
የ35 ዓመቱ አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ የቀድሞውን የውድድሩን ክብረ ወሰን በአራት ደቂቃዎች በማሻሻል ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።
አትሌቱ በአውሮፓውያኑ 2023 በሻንጋይ ማራቶን በኬንያዊው ፊሊሞን ኪፕቹምባ ተይዞ የነበረውን የ2:05:35 ሰዓት በመስበር በቻይና በማራቶን ውድድር የተመዘገበ የምንጊዜም ፈጣኑ ሰዓት ባለቤት መሆን ችሏል።
በውድድሩ አትሌት ታምራት ቶላ ለአንደኛ ደረጃ የተዘጋጀውን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፤ የቦታውን ክብረወሰን በመስበሩ ተጨማሪ 60 ሺህ የቻይና ዩዋን ጨምሮ በአጠቃላይ ወደ 59 ሺህ ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ሽልማት ተረክቧል።
በሌላ በኩል በሴቶች በተካሄደው ውድድርም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አንቺንአሉ ደሴ በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በማጠናቀቅ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የቤጂንግ ማራቶን አሸናፊ በመሆን የ50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ መሆናኗን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ! #BeijingMarathon #Ethiopian #Athletics #World #Champions
6
1October 18, 2026 2K 1



