8ቱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች፤ ✅ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣… — Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ — TG.ME

8ቱ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች፤

✅ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የሚያሻግር፣ ወዳጆችን በማበራከት የሚተጋ፣ የደመኝነት ዕይታ ያላቸውን ደግሞ የሚመክር፣ ለቀጠናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ቅድሚያ የሚሰጥ፣ ተነሳሽነቶች ያሉትና ዓለም አቀፍ ተቀባይነታችንን የሚያሳድግ ይሆናል፤

✅ ጥራትን መሠረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲኖር ይደረጋል፤

✅ ትምህርት፣ ጤና እና ማኅበራዊ ጥበቃን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከሉ ያደረገ ልማት ይፋጠናል፤

✅ ለዕድገት ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንደስትሪና የግብርና ግብአቶች ዘመናዊ የመሠረተ ልማት ግንባታ ዐቅማችን ራሱን እንዲችል ይደረጋል፣

✅ የፕሮጄክትና የፕሮጄክት ፋይናንስ አፈጻጸምን ዘመናዊ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ይሠራል፤

✅ የታክስ መሠረትን በማዘመን፤ የመንግሥት ገቢና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር ዐቅም ያድጋል፤

✅ በፌዴራል መንግሥትና በክልሎች መካከል ያለው የሥራ ቅንጅትና አፈጻጸም የተባበረ፣ የተደጋገፈ፣ ቀልጣፋና እንከን አልባ እንዲሆን ይደረጋል፤

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ስምንት የ2019 ዓ.ም ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች አሰቀምጠዋል። ሰላም ለኢትዮጵያ ዕድገትና ግስጋሴ ያለውን ዋጋ ያጤነና ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ኅብረትን፣ ትብብርንና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር የሚከናወን ይሆናል ሲሉም በንግግራቸው ገልጸዋል።
#የመደመር_መንግሥት #ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ! #Ethiopia #Medemer #diplomacy
👍1
October 6, 2026 1.2K 3