በየደረጃው የሚታቀዱ የሕብረተሰብ ጤና ተግባራት ተቀናጀው በመስራት የጤና ስርዓቱን የሚገነቡ መሆን እንዳለባቸው… — Ethiopian Public Health Institute | የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት — TG.ME

በየደረጃው የሚታቀዱ የሕብረተሰብ ጤና ተግባራት ተቀናጀው በመስራት የጤና ስርዓቱን የሚገነቡ መሆን እንዳለባቸው ተገለጸ
-------------------------------------
የኢንስቲትዩቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ ከክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶችና ጤና ቢሮዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የእቅድ ማናበብ አውደ ጥናት ከነሐሴ 21 እስከ 23/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እያካሄደ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በተዋረድ በክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች መካከል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በክልሎች የተካሄደውን የእቅድ አፈጻጸም ክትትል እና ግምገማ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ተግባራት እቅድን ለማናበብና የተሻሉ ውጤቶችን ለማስመዝገብ የሚያስችል የቀናጀ የጋራ እቅድ ለማዘጋጀት ነው ታስቦ በመካሄድ ላይ ያለ መድረክ ነው፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አማር ባርባ፣ የኢንስቲትዩቱን ዋና ዳይሬክተርን በመወከል እንደተናገሩት በአገር አቀፍ ደረጃ የሕብረተሰብ ጤናን ለማስጠበቅ የሚከናወኑ በርካታ ተግባራት የተሳሰሩና በቅንጅት የሚሰሩ የሕብረተሰቡን ጤና በማስጠበቅ ደረጃ የተሻሉ ውጤቶች የሚመዘገብባቸው መሆን እንዳለባቸውና የእቅድ መናበብ ስራውም በቀጣይ በጀት ዓመት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ በአንድ የጋራ ብሔራዊ እና ክልላዊ የሕብረተሰብ ጤንነት በማስጠበቅ የሚለካ እቅድ ላይ የተመሰረተ እንዲሁም የተሻለ የሕብረተሰብ ጤና ስርዓት የሚገነባ መሆን አለበት፡፡

ወ/ሮ ህይወት አበበ የኢንስቲትዩቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በበኩላቸው በዚህ በጀት ዓመት በተካሄደው የተቀናጀ የእቅድ ክትትልና ግምገማ መሰረት የተመዘገቡ ጠንካራና ውጤታማ ስራዎቻችን ላይ መሰረት በማድረግ እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን ለማረም በሚያግዝ ደረጃ የተቀናጀና የተናበበ ብሎም የሕብረተሰቡን ጤና በተሻለ ለማስጠበቅ ተግባራዊ እቅድ ለማዘጋጀት ልዩ ትኩረት የተሰጠው አውደ ጥናት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሁሉም የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተካሄደው የተቀናጀ የእቅድ ክትትል ግምገማ ሪፖርት በመድረኩ ቀርቦ ሰፊ ውይይት እየተካሄደበት ሲሆን ለበጀት ዓመቱ ለሚዘጋጀው ተግባራዊ እቅድ እንደ ወሳኝ ግብአት እያገለገለ ሲሆን ወጥና የተናበበ የጋራ አቅድ ለማዘጋጀት የክልል ጤና ቢሮ እና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊዎች እንዲሁም ተወካዮች በአውደ ጥናቱ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
August 27, 2026 2.5K 1