አላህ ሆይ በይፋ እመሰክራለው:- ካንተ ውጭ በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም፡፡ አንድ ነህ፡፡ አጋርም… — Best Amharic Neshida be kb — TG.ME

አላህ ሆይ በይፋ እመሰክራለው:- ካንተ ውጭ በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም፡፡ አንድ ነህ፡፡ አጋርም የለህም፡፡ ንግሥና ያንተ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ ላንተ ብቻ ነው፡፡ አንተ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ›› አላህ ሆይ የአለማቱ ብቸኛ ፈጣሪ እና አስተናባሪ ለስልጣንህ ተጋሪ እና ሸሪክ የሌለህ ኃያል ጌታ ነህ በእዝነትህ ለእኛ ደካማ ባሮችህ በዚህ በተባረከ ቀን መልካምን ሁሉ አድርግልን ፤ ውዴታህንም ለግሰን ፤ ወንጀላችንን ማረን ኢላሂ ለበይክ ላሉህ ባሮችህ ሁሉ መቅቡል የሆነ ሀጅን ወፍቃቸው፤ ለኛም ቤትህን ለናፈቅነው ባለንበት እዝነትህን ወፍቀን አላህ ሆይ! ዱዓ ባደረግንበት አንተ በመረጥክልን መልካም ነገር ተፅፎልን ቢሆን እንጂ የአረፋ ፀሀይ አትጥለቅ አላህ ሆይ! እራሳችንን ከእሳት ነፃ ሳታወጣን ፣ ጀነትን ለኛም፣ ለወላጆቻችን ለምወዳቸውና ለሁሉም ሙስሊም ሳይወፈቅ የአረፋ ፀሀይ አታጥልቃት አላህ ሆይ! ከምንመኘው የተሻለ ህይወት ተፅፎልን ቢሆን እንጂ የዐረፋ ፀሀይ የምትጠልቅ አታድርገው ጌታችን ሆይ! አንተ በእኛ ላይ የዋልክልን ችሮታ ምንኛ ላቀ፡፡ አንተ ሀመሪና አዛኝ የሆነከው ጌታችን ምህረትህን ለግሰን አንተ ካልማርከን እኛ ከንቱ ፍጡራኖች ነንና፡፡ ከደጋግ ባሮችህም ታደርገን ዘንድ እንማፀንሀለን፡፡ አንተን አብዝተው ከሚያወድሱህና ከሚያጥራሩህም ባሮችህ አድርገን፡፡ አንተ አሸናፊና ጥበበኛ ጌታ ነህ፡፡ ኢላሂ ከንግግራችን ይልቅ ተግባራችን ያመዝን ዘንዳ አንተ እርዳን ፤ አንተን የምትፈራ ልብም ስጠን አላህ ሆይ ዓይኖቻቸው ባንተ ፍራቻ ከተሞሉት፣ የዱኒያ ህይወታቸው አንተን በማስታወስ ከተባረኩት፣ ልባቸው ባንተ ውዴታ ከተሞሉት ፣ የአኼራ ህይወታቸው በእዝነትህ እና በምህረትህ ከሚያጌጡት፣ በጀነትህ ውስጥም አንተን እና ውዱ ነብይህን በአይናቸው ከሚመለከቱት ባሮችህ አድርገን አላህ ሆይ! ፀጋህ እንዳይነሳብን፣ ጤናችን እንዳይወገድ፣ ከድንገተኛ ቅጣትህ፣ ከሁሉም ቁጣህ (ቅጣትህ) ባንተ እንጠበቃለን ኢላሂ በዛሬው የአረፋ ቀን ተቀባይነትን ከሚያገኙት ፤ ዱኣቸው ከማይመለስባቸው ባሮችህ መካከል አድርገን፣ መቋረጥ የሌለውን ሰፊ ሲሳይ፣ መዘጋት የሌለበትን የጀነት በሮችህን ክፈትልን ለስልጣንህ ተጋሪ የሌለው ጌታችን ሆይ:- የተናናሽ ለማኞችን ልመና እንማፀንሀለን፣ በዛሬዋ ቀን በብዛት ባሮችህን ከእሳት ነፃ በምታወጣበት ቀን እኛንም በእዝነትህ ከእሳት ቅጣት አውጣን ኢላሂ ለማንም ያልነገርነውን ሀጃችንን ላንተ ብቻ ነግረንሀልና ሀጃችንን ፈፅምልን ያ ረህማን ጤና አጥተው ለሚሰቃዩት ሁሉ የመዳንን ካባ አልብሳቸው፣ ሙሉ የሆነችን ምህረት አድርግላቸው በወንጀል ማእበል ሰጥመው እዝነትህን ተስፋ አድርገው ወዳንተ መመለስ ለሚሹት ሁሉ በእዝነትህ ወደ ቤትህ መልሳቸው፣ ዳግም መመለስ የሌለበትን መመለስ ወዳንተ መልሳቸው አላህ ሆይ አባታችን አደም እና ሀዋን በአረፋ ተራራ እንዳገነኘህ ሁሉ በስደት አለም የቤተሰብ ናፍቆት የሚያሰቃያቸውን ሙራዳቸው ሞልቶ ከናፈቃቸው ቤተሰብ የሚገናኙ አድርጋቸው ያ ረህማን ቁርኣን የህይወታችን መመሪያ፣ ሰላት የቀልባችን መርጊያ አድርግልን ኢላሂ በዱኒያ ህይወታቸው አግኝተው ላጡት ሁሉ ምርጥ ምትክን ተካላቸው፣ የሰው ፊት ከማየት ታደጋቸው፣ በስደት በረሃብ ቸነፈር ለሚገረፉ ፍጡራኖችህ ሁሉ እዘንላቸው ያ ሰመዱ መጠጊያ አጥተው ለሚሸሹት ሁሉ መጠጊያ ሁናቸው፣ ጥላ ከለላ ሁናቸው ያ ሰላሙ አንተ ሰላም ነህ፤ ሰላምም ካንተ ነው:: ሀገራችንን ሰላም አድርግልን፣ በፍልስጤም፣ በሱዳን ፣በሊቢያ ሰቆቃ ላይ ያሉትን ባሮችህ ሁሉ ታደጋቸው ኢላሂ ከሞት ስቃይ፣ ከቀብር ቅጣት ጠብቀን፣ በፍርዱ ቀንም የቀኝ ጓዶች ከሚሆኑት አድርገን:: የውዱን ነብይህን ሀውድ ከሚጠጡት ባሮችህ አድርገን አሚን

May 26, 2026 19K 3 25