ልባችሁ ውስጥ የዩሱፍ ታሪክ ያለ አይመስላችሁም? ሩ... ቅ ህልሞች፣ አጥር የተሻገሩ ምኞቶች... እና ደግሞ "ዩሱፍ ሊመለስ አይችልም" ብለው የሚምሉ የመንደሩ ሰዎች አሉ፡፡ የያዕቁብን የለቅሶ ዓለም እንደ ንጭንጭ የሚቆጥሩ ዘላኖች አሉ፡፡ በህይወት ኖረም አልኖረም ለሩቅ ሰዎች በባርነት እንደሸጡት እርግጠኛ የሆኑ ወንድሞቹም አሉ፡፡ አንዳንዴ... እዚህ መሀል ነው የአላህ ፍላጎት ጣልቃ የሚገባው፡፡ ''የማይሆን" ብለው የማሉለት ጉዳይ መሀል "የፈለኩትን አድራጊ ነኝ'' ሊል ይመጣል። ሊቀየር የማይችል የሚመስለን ሁሉ ይቀየራል፡፡ ተበትነው የነበሩ ምኞቶች ይሰበሰባሉ፡፡ ህልም የነበረው በገሀዱ ዓለም ይታያል፡፡ አጠገብህ ላሉት ሰዎችም "አላህ እንደሚቀበለኝ በእርግጠኝነት ምዬ አልነገርኳችሁም ወይ?'' ትላቸዋለህ፡፡ እናም ዱዓችን ተቀባይነት የሚሆንበት ቀናቶች ላይ ነን እንበርታ ...... (@ ከ fb መንደር የተወሰደ)
March 10, 2026 25.3K 1 23