ሰበር ዜና በሳዑዲ ዓረቢያ የረመዳን ወር ጨረቃ መታየቷ ተረጋገጠ! ሀሩን ሚዲያ፤ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ል የሳዑዲ ዓረቢያ የቴሌስኮፕና የአስትሮኖሚ ባለሙያዎች የረመዳን ወር ጨረቃ መታየቷን በይፋ አብስረዋል። በዚህም መሠረት ነገ ረቡዕ የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ል. የታላቁ የረመዳን ወር የመጀመሪያ ቀን ሆኖ ይውላል። ይህንን ተከትሎም ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ል. ምሽት ጀምሮ በሁለቱ ቅዱሳን መሳጂዶች (መካና መዲና)፣ በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ መሳጂዶች የረመዳን ወር ልዩ ሶላት የሆነው የተራዊህ ሶላት መከናወን ይጀምራል። ሀሩን ሚዲያ ለመላው ሙስሊም ማኅበረሰብ እንኳን ለ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ ታላቁ የረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤ ወሩ የኢባዳ፣ የእዝነትና የሰላም እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል። ረመዳን ሙባረክ!
58
4
4
1
1February 17, 2026 23.6K 2 22