Ethio_E_learning_center_Grade 9-10: post #585 — TG.ME

Forwarded fromISI S

የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ተራዝሞ የቆየው የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዝናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። በመጀመሪያ ዙር የተሰጠው የ12ኛ ክፍል የስነዜጋና ስነምግባር ትምህርት የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል መወሰኑንም ኤጀንሲው ገልጿል። ተማሪዎችም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን http://Result.neaea.gov.et ማየት እንደሚችሉ ጠቁሟል። የፈተና እርማቱ ደህንነታቸው አስተማማኝ በሆኑና ከንክኪ ነጻ በሆኑ የማረሚያ ማሽኖች አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ በፌደራል ፖሊስና በሴኩሪቲ ካሜራዎች ታግዞ በጥንቃቄ መከናወኑንም ነው የገለጸው።

👍15❤3
February 23, 2022 13.8K 7