Forwarded fromETHIO GAT 📝//FX
የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ለአገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በፈተና ጣቢያነት ባለመካተታቸው ቅሬታ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማቅረባቸው ተሰምቷል፡፡ አገልግሎቱ ቅሬታ ላቀረቡ ዩኒቨርሲቲዎች በሰጠው ምላሽ፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች በፈተና ጣቢያነት ያልተመረጡት ከፌዴራል ተቋሙ የማስፈፀም አቅም ውስንነት ጋር በተያያዘ መሆኑን ገልጿል፡፡ "ፈተናውን ለማስፈፀም ከማዕከል የሚጠቀሟቸው አስተባባሪዎች እና የፌዴራል ፖሊስ ፀጥታ ኃይሎች ማሰማራት የማይችልባቸው ሁኔታዎች ስላሉ ብቻ" የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች በፈተና ጣቢያነት አለመካተታቸውን አገልግሎቱ አስረድቷል፡፡ የ NGAT ምዝገባ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሲከናወነ መቆየቱ ይታወሳል። አሁን ላይ የተወሰኑ ተፈታኞቹ ወደ ሌሎች ዩነቨርሲቲዎች እንዲዘዋወሩ መደረጉ ታውቋል፡፡ በመሆኑም ተፈታኞች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉና በተመደቡበት አቅራቢያ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ አገልግሎቱ ጥሪ አድርጓል፡፡ አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር
5August 21, 2026 2.3K 2