አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባ ተማሪ ምክር ቢጠይቀኝ የምነግረው 9 እውነታዎች! 90% የሚሆኑ ተማሪዎች ሳያውቁ… — Ethiopian Exit Exam ➕crypto, Jobs For Fresh Graduates for the memory of procuter habtamu🇪🇹 — TG.ME

አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባ ተማሪ ምክር ቢጠይቀኝ የምነግረው 9 እውነታዎች! 90% የሚሆኑ ተማሪዎች ሳያውቁ ወይም ሳያስተውሉ የሚሰሯቸውን ስህተቶች ለማስቀረት እና የዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁን ስኬታማ ለማድረግ እነዚህን ቀላል ግን ወሳኝ ምክሮች ተግበሩ👇 1. የመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤት (GPA) ላይ ትኩረት ማድረግ    የመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤት አንዴ ከወረደ በኋላ በቀጣዮቹ ሴሚስተሮች መልሶ ማስተካከል በጣም ከባድ ነው፤ ምክንያቱም አጠቃላይ ውጤታችሁ የሚሰላው በየ ሴሚስተሩ ያገኛችሁ ውጤት እየተደመረ ስለሆነ የሚሄደው ። ስለዚህ Freshman ላይ ሳትዘናጉ፣ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ትኩረት ሰጥታችሁ እና በስነ-ስርዓት አጥንታችሁ ጥሩ ውጤት አስመዝግቡ። 2. ማንነትን አለመቀየር    ገና ግቢ እንደተገባ ታዋቂ ለመሆን ወይም ከልክ በላይ ለመታየት ከመሞከር ይልቅ ትሑት መሆን ይበልጣል። ተፈጥሯዊ ማንነታችሁን ሳትቀይሩ፣ ሰውን ሳትንቁ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ መግባባት እና ሰላማዊ ግንኙነት መፍጠር የተሻለ ነው። 3. ጓደኞችን በጥንቃቄ መምረጥ    በዩኒቨርሲቲ አብረዋችሁ የሚበሉ፣ የሚውሉ እና በአንድ ክፍል ውስጥ የሚኖሩ ጓደኞች በህይወታችሁ እና በትምህርታችሁ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አላቸው። ጥሩ ጓደኛ ወደ ላይ ያወጣችኋል፣ መጥፎው ደግሞ ይስባችኋል። ስለዚህ ህልማችሁን እና ትምህርታችሁን የሚደግፉ ሰዎችን በጥንቃቄ ምረጡ። 4. የግሩፕ አባላትን በጥንቃቄ መምረጥ    በአሳይመንት፣ በፕሮጀክት እና በግሩፕ ስራዎች ጊዜ ለትምህርት ጥሩ አመለካከት እና ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች መምረጥ አለባችሁ። አለበለዚያ ስራ የማይሰሩ ሰዎችን አቀላቅላችሁ የቡድኑን ስራ በሙሉ በእናንተ ላይ የሚጥሉ እና ውጤታችሁን የሚያበላሹ አባላት ያጋጥሟችኋል ።የ ግሩፕ ስራ የ final ፈተና ላይ ስለሆነ አብዋኛውን ጊዜ የምታስገቡት ለ ፈተናው መዘጋጀት ትታችሁ Assignment ላይ ነው ጊዚያችሁን የምታሳልፉት፣ ሰው ምረጡ! ​ለምታስቡላቸው ጓደኞቻችሁ Share አድርጉት! ​👍🏽 ለቀጣይ ክፍሎች React ማድረጋችሁን አትርሱ!

❤13👏2
August 13, 2026 3.9K 1 9