Ethiopian Education: post #4655 — TG.ME

ስህተትን አምኖ መቀበል በህይወት ውስጥ ትልቁ ዋጋ ያለው በጭራሽ አለመውደቅ ላይ ሳይሆን፣ በወደቅን ቁጥር መነሳት መቻላችን ላይ ነው።                   ኔልሰን ማንዴላ ስህተት መስራት በማንም ሰው ህይወት ዉስጥ ያለና የተለመደ ነገር ነው። ስኬታማና ተጽኖ ፈጣሪ የሆኑ ሰዎች ፣ ከስህተታቸው የተማሩ ሰዎች እንጂ ምንም ስህተት ያልሰሩ ሰዎች አይደሉም። ህይወትህ ውስጥ ስህተት ሠርተህ ከሆነ፣ አምነህ ተቀበለው። ስህተትን አምኖ መቀበል  ደካማነት  ሳይሆን፣  ለለውጥ የመጀመሪያው እርምጃ  ነው። ​ምንም የተበላሸ ነገር እንደሌለ በማስመሰል ህይወትን ማስተካከል አይቻልም። ልናምነውና ልንቀበለው የማንፈልገውን ነገር ልናርም አንችልም።  እውነታውን በመካድ ውስጥ ሆነህ በእውነት አዲስ ምዕራፍ መጀመር አትችልም። ስላደረግከው ነገር አታስመስል።ፊት ለፊት መጋፈጥን ልመድ ፣ ከእሱም ተማር ፣ ኃላፊነቱን ውሰድ ፣ከዚያም ወደፊት ቀጥል። ​ ስህተትህ ያደረግከው አንድ ድርጊት እንጂ ማንነትህ አይደለም። ስለዚህ አምነህ ተቀበለው ፣ ከእሱ ተማር  ፣ ለውጠው፣ እንደገና ጀምር። ​

❤6👏5
August 28, 2026 1.6K 1 8