ክፍል 16 በትክክለኛ ሰዎች ራስህን ክበብ “ብዙ ጊዜ አብረሃቸው ከምታሳልፋቸው አምስት ሰዎች አማካይ ነህ።” — ጂም ሮን ጓደኞችህ ሰነፎች ከሆኑ፣ አንተም ሰነፍ ትሆናለህ። ጓደኞችህ ነገሮችን ማዘግየት የለመዱ ከሆነ፣ አንተም ነገሮችን ማዘግየት ትጀምራለህ። ጓደኞችህ በትጋት የሚሰሩ ከሆኑ፣ አንተም በትጋት መስራት ትጀምራለህ። ጓደኞችህ መጽሐፍ ማንበብ የሚወዱ ከሆነ፣ አንተም መጽሐፍ ማንበብ ትጀምራለህ። በዙሪያው ያለው ከበባ ተጽዕኖ የማያደርስበት ሰው ሊኖር ይችላል፣ ግን ይህ በጣም አልፎ አልፎ ነው። ብዙ ሰዎች ሰነፍ የሚሆኑት አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፉት ከሰነፎች ጋር ስለሆነ ነው። ከአንተ ጋር በጣም ቀርበው የሚኖሩ ሰዎችን ልማዶች ትወስዳለህ። የእነሱ ጥሩም ሆነ መጥፎ ልማዶች የአንተ ልማዶች ይሆናሉ። ለምሳሌ፣ ጓደኛህ ጊዜውን ማባከን የሚወድ ከሆነ፣ አንተም ከእሱ ጋር ጊዜህን ማባከን ትጀምራለህ። በሌሎች ሰዎች ተጽዕኖ አለመውሰድ በጣም ከባድ ነው። ስለዚህ ማድረግ አለብህ? ማድረግ ያለብህ ብቸኛው ነገር መንቃት ነው። ስንፍናንና ነገሮችን ማዘግየትን ማሸነፍ የምትችለው በመንቃት ብቻ ነው። ስለምታደርጋቸው ነገሮች በጣም ንቁ መሆን አለብህ። “አይ” ማለትን መማር አለብህ። በተቃራኒው ደግሞ ሰነፍ ያልሆኑ፣ ነገሮችን የማያዘገዩ እና ጥሩ ልማዶችን የያዙ ጓደኞች ካሉህ፣ አንተም እንደነሱ ትሆናለህ። ምርጫው ያንተ ነው። በዙሪያህ የምታደርጋቸው ሰዎች በሕይወትህ ላይ እጅግ ትልቅ ተጽዕኖ ይኖራቸዋል። አስተሳሰብህን፣ ድርጊቶችህን እና ሕይወትህን ይቀርጻሉ። ትክክለኛ ሰዎች ሕይወትህን ያሻሽላሉ፤ ትክክል ያልሆኑ ሰዎች ደግሞ ሕይወትህን ያበላሻሉ። ሁልጊዜ አሉታዊ አስተሳሰብ ካለው ሰው ጋር የምትቆይ ከሆነ፣ እሱም አንተን አሉታዊ ሰው ሊያደርግህ ይችላል። በምትኩ ግን በአዎንታዊ ሰዎች ከተከበብክ፣ አንተም አዎንታዊ ሰው ትሆናለህ። ስለዚህ በዙሪያህ ስላሉት ሰዎች በጥልቀት ማሰብ አለብህ። አስተሳሰብህን ለመቀየር የከበቡህን ሰዎች ቀይር አስተሳሰብህን መቀየር ከፈለግህ፣ የምታደርገውን ነገር ሁሉ መቀየር አለብህ። በዙሪያህ ያሉ ሰዎችን መቀየር አለብህ። አብዛኛውን ጊዜ የምታሳልፈው ሰዎች ሰነፎች፣ አሉታዊ እና ሕይወትህን በትንሹም ቢሆን የማያሻሽሉ ከሆኑ፣ የከበቡህን ሰዎች መቀየር ወይም ቢያንስ ምክራቸውን ማዳመጥ መቀነስ ጠቃሚ ነው። አንድ ሰው እንዲህ ብሏል፦ “የሚጎዳህን መስኮት ዝጋ፤ እይታው ምንም ያህል ውብ ቢሆንም።” እኔም ይህ በጣም ተሰምቶኛል! ከሁሉም ሰው ምክር አትቀበል ከእሱ ጋር ቦታ መቀያየር ከማትፈልገው ሰው በሕይወትህ ላይ ምክር እንዲሰጥህ አትፍቀድ። ለምሳሌ፣ እንዴት ደስተኛ መሆን እንደምትችል ምክር ከፈለግህ፣ ይህንን ምክር መጠየቅ የሌለብህ ሰው ቢኖር ደስተኛ ያልሆነ ሰው ነው። አስብበት እስኪ ፤ የእሱ ምክር በእውነት ዋጋ ያለው ከሆነ፣ እሱ ራሱ ለምን ደስተኛ አይደለም? ማንም ሰው ለዘላለም ደስተኛ ሳይሆን መኖር አይፈልግም። ምክር የምትቀበልበት ሰው የምትኖረውን ሕይወት ይወስናል። ደስተኛ ካልሆኑ ሰዎች ምክር ከተቀበልክ፣ አንተም ደስተኛ አትሆንም። ጤናማ ካልሆኑ ሰዎች ምክር ከተቀበልክ፣ አንተም ጤናማ ያልሆነ ሰው ትሆናለህ። ቁጡ ከሆኑ ሰዎች ምክር ከተቀበልክ፣ አንተም ቁጡ ትሆናለህ። “የምትፈልገው ነገር ከሌላቸው፣ የሚናገሩትን አትስማ።” — አሌክስ ሆርሞዚ መሆን ከማትፈልገው ሰው ምክር መቀበልን አቁም። ሕይወትህን እንዴት መኖር እንዳለብህ እና ምን ማድረግ እንዳለብህ ሌሎች ሰዎች የሚሰጡህን አስተያየት ማዳመጥ አቁም። ምክራቸው ለአንተ ምንም ጥቅም የለውም። ሕይወትህ የአንተ ነው፤ ስለዚህ በራስህ መንገድ ኑር። ይቀጥላል...
12
6
6
1