Ethiopian Education: post #4642 — TG.ME

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የምዝገባ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ ምረቃ መደበኛ (በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሃ-ግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከዚህ በታች በተጠቀሱት ቀናት እና መስፈርቶች መሠረት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። አስፈላጊ መስፈርቶች እና ቀናት * የምዝገባ ቀን፡ ከነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ። * መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡     * በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው  (COC) ያለፉ * የመግቢያ ፈተና (UAT) የሚሰጥበት ቀናት ከጳጉሜን 02 እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከማመልከቻ ጋር በተያያዘ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የሚከተሉትን ሊንኮች ይጫኑ 1.  ለ አጠቃላይ የቅድመ ምረቃ ማመልከቻ 2.  ለቅድመ ምረቃ ለቀን መደበኛ መርሃ ግብር ትምህርት አመልካቾች: 3.  ለቅድመ ምረቃ ለማታ ተከታታይ መርሃ ግብር ትምህርት አመልካቾች፡ 4. ለ ልዩ ፕሬዝዴንሻል የስኮላርሺፕ የትምህርት እድል፤ 5.  ለ ልዩ የስኮላርሺፕ እድል ለመምህራን ትምህርት፡ * ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ:- https://admission.aau.edu.et Share to grade 12 students

❤12
August 25, 2026 3.5K 16