Ethiopian Education: post #4634 — TG.ME

Blood Grouping (የደም አይነትን መለየት) Blood grouping is the process of determining a person's blood group by identifying the antigens present on the surface of red blood cells (RBCs). የደም አይነትን መለየት ማለት በቀይ የደም ህዋሳት ዉስጥ ያሉትን አንቲጂኖችን(antigens) በመመርመር የሰዉን የደም አይነት መወሰን ነዉ። There are two main blood grouping systems : ሁለት ዋና ዋና   የደም አይነት መለየ መንገዶች አሉ ። 1. ABO blood grouping system and (ABO የደም አይነት መለየ መንገድ) እና 2. RH blood group system. (RH የደም አይነት መለየ መንገድ 🖍  ABO blood grouping system determines the presence or absence of antigen A ,  B ,or both and their corresponding antibody in there plasma. ABO የደም አይነት መለየ መንገድ የአንቲጂን A ፣ B ወይም የሁለቱንም መኖርንና አለመኖሩን እና የደም ፕላዝማ ውስጥ የእያንዳንዳቸውን ፀረ አንቲጂን የምንለይበት ዘዴ ነው። Ex. ✍️   Blood group A has antigen A ,and anti B antibody ✍️ Blood group B has antigen B and abti A antibody ✍️ Blood group AB has both antigen A and B, but no anti-A & anti B antibodies . ✍️ Blood group O has no A or B antigen ,but has has both anti A and anti B antibodies. ለምሳሌ ✍️ የደም አይነት A አንቲጂን A እና የአንቲጂን B ማጥፊያ ፀረ B አለው ። ✍️የደም አይነት B አንቲጂን B እና የአንቲጂን A ማጥፊያ ፀረ  A አለው ። ✍️ የደም አይነት AB አንቲጂን A እና B አለው ፣ ነገር ግን የአንቲጂን A ም ሆነ የአንቲጂን B ማጥፊያ ፀረ Aም ፀረ Bም የለውም። ✍️ የደም አይነት O ደግሞ አንቲጂን Aም አንቲጂን Bም የለውም ፣ ነገር ግን የሁለቱም ማጥፊያ ፀረ A እና ፀረ B አለው። 🖍 RH blood group system determines the presence or absence of antigen D. If antigen D is present , it is RH positive(RH +) If antigen D is absent it is RH negative (RH -) RH የደም አይነት መለየ መንገድ የአንቲጅን D መኖሩንና አለመኖሩን የምንለይበት መንገድ ነው። አንቲጂን D ካለው RH positive ነው ። አንቲጂን D ከሌለው RH negative ነው ። ስለዚህ አንድ ሰው የ ደም አይነቱ A ሆኖ አንቲጂን D ካለው ...A+ ይባላል ፣ የደም አይነቱ A ሆኖ አንቲጂን D ከሌላው ...A- ይባላል ማለት ነው።  በዚህ መሠረት ሌሎቹም የደም አይነቶች    A+, A- , B+, B- , AB+, AB-, O+, O- በመባል ይከፋፈላሉ። Short note #from Grade 10 biology(unit 5)

❤12🙏1
August 21, 2026 3.3K 12