በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለመፈተን የሚስፈልጉ፦ ➫ ማንኛውም… — Coc and exit exam info. — TG.ME

#በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለመፈተን የሚስፈልጉ፦

➫ ማንኛውም ተመዛኝ የብሔራዊ መታወቂያ እና የትምህርት ማስረጃ ስካን አድርጎ ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡

➫ በድጋሚ ፈተናውን የምትወስዱ ተመዛኞች መረጃችሁን ከምዝገባ በፊት ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

➫ አዲስ ተመዛኞች የስም ዝርዝራችሁ ከተማራችሁበት ተቋም ሲላክ በስልክ ቁጥራችሁ የጤና ሚኒስቴር መለያ ቁጥር ስለሚላክላችሁ እሱን በመጠቀም መረጃችሁን ማያያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡

➫ አዲስ ተመዛኞች ስማችሁን ሲስተም ላይ ካጣችሁት ከተቋማችሁ ማስላክ ትችላላችሁ፡፡

በምዝገባ ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በነጻ የስልክ መስመር 952 በመደወል ከዚያም 3 ቁጥርን በመጫን በቀጥታ እገዛ ማግኘት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@ethiococandexitexam
@ethiococandexitexam
❤7👍1🙊1
April 30, 2026 6.5K 22