እንኳን ደስ ያላችሁ‼️ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በአማካይ ውጤታቸው 49.50 - 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ የሚጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፥ ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ ያሟሉ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል። በመሆኑም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስተሩ ገልፀዋል። 💥 ከ297/600 ያመጣቹህ ተማሪዎች አልፋቹኋል 👏 For more 👉 @Ethio600 👉 @Ethio600
40
8
7
5
3September 30, 2025 22.6K 21