የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዲጂታል ገንዘቦች እና በቨርቹዋል ሀብቶች ዝውውር ላይ ጥብቅ እገዳ ጣለ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በህግ ከተፈቀደው ውጪ በማናቸውም የቨርቹዋል ሀብቶች ግብይት ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ።
እገዳው ቢትኮይንን ጨምሮ ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎችን ብቻ ሳይሆን፣ ለማንኛውም ክፍያና ኢንቨስትመንት የሚያገለግሉ በዲጂታል መልኩ የሚተላለፉ መግለጫዎችንም ያካትታል።
በተለይም የሚከተሉት ተግባራት ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው ብሏል ባንኩ;
👉በቨርቹዋል ሀብት እና በመደበኛ ገንዘብ መካከል የሚደረግ መመንዘር
👉በቨርቹዋል ሀብቶች መካከል የሚደረግ ልውውጥና ዝውውር
👉የቨርቹዋል ሀብቶችን ማስቀመጥ፣ ማስተዳደር እና የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት
ህብረተሰቡ ከህጋዊ ተጠያቂነት፣ ከማጭበርበር፣ ከሳይበር ጥቃት እና ከከባድ የገንዘብ ኪሳራ ለመጠበቅ ከነዚህ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ ባንኩ አሳስቧል።
#Join👇👇
👉@Tech_News_ethio
👉@Tech_News_ethio

1July 26, 2026 194