👉በምስሉ ላይ እንደሚታየው ለስላብ ኮንክሪት ማፍሰሻ ዝግጅት ከእንጨት ሰሌዳዎች ይልቅ Plywood Sheets በጥራት ተዘርግተው ከላይ የቢም እና የስላብ ብረቶች እየተዘጋጁ ይገኛሉ።
📌 በምስሉ ላይ የሚታዩ እና የፕላይዉድ ዋና ዋና የምህንድስና ጥቅሞች፦
🔹 Smooth Concrete Surface (ልሙጥ ኮንክሪት)፦ ፕላይዉድ መጠቀም የኮንክሪቱ የታችኛው ክፍል (Soffit) በጣም ልሙጥ ሆኖ እንዲወጣ ያደርጋል፤ ይህም ከኮንክሪት በኋላ የሚሰራውን የፕላስተር ወጪ በእጅጉ ይ ቀንሳል።
🔹 Watertight Joints (የሲሚንቶ ውኃ አለመፍሰስ)፦ የፕላይዉድ ሉሆች ሰፊና እኩል በመሆናቸው በመካከላቸው ያለው ክፍተት በጣም አነስተኛ ነው፤ ይህም የሲሚንቶ ውኃ (Cement Slurry Leaks) እንዳይፈስ ይከላከላል።
🔹 Speed & Efficiency in Construction፦ በትናንሽ የእንጨት ሰሌዳዎች ከሚሰራው ይልቅ በትልልቅ የፕላይዉድ ሉሆች ፎርምወርክ ማንጠፍ የሳይት ስራውን በጣም ፈጣንና ቀልጣፋ ያደርገዋል።
⚠️ ለጥራት እና ለደህንነት የሚረዱ ወሳኝ የሳይት ማስታወሻዎች፦
1️⃣ Form Oil / Mold Release Agent፦ ኮንክሪት ከመፈሰሱ በፊት በፕላይዉዱ ላይ የፎርምወርክ ዘይት (Form Release Oil) መቀባት ፕላይዉዱ ከኮንክሪት ጋር እንዳይጣበቅ እና በቀላሉ እንዲነሳ ይረዳል።
2️⃣ Sealing Edge Joints፦ በፕላይዉድ ሉሆች መካከል ያሉትን ጥቂት ክፍተቶች በማስኪንግ ቴፕ ወይም በፎም (Tape/Foam) ማሸግ የሲሚንቶ ውኃ ፍሰትን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል።
3️⃣ Reusability & Care፦ ፎርምወርክ በሚነቀልበት ጊዜ ፕላይዉዱ እንዳይሰባበር ጥንቃቄ ማድረግ፤ በጥሩ ሁኔታ ከተያዘ ለበርካታ ጊዜያት (Multiple Reuses) ማገልገል ይችላል።
@etconp

6September 13, 2026 1.9K 8