ሚዛን እና ምጣኔ በኪነህንጻ (Scale and Proportion) የ ዘለቀ በላይ ንድፎች 🌟ዘለቀ ንድፎቹን… — Ethiopian Construction Vacancy & Tender — TG.ME

👉ሚዛን እና ምጣኔ በኪነህንጻ (Scale and Proportion) የ ዘለቀ በላይ ንድፎች

🌟ዘለቀ ንድፎቹን ከተለመደው መደበኛ የሚዛን እና ምጣኔ መስፈርቶች በማስፈንገጥ ንድፉ አጫዋች እና ቀልብ ሳቢ እንዲሆን ማድረግ ችሏል። 

በዚህም ምክንያት ንድፎቹን ግዝፈት ለመረዳት የግዴታ ሰው፣ ተሽከርካሪ ወይንም እጽዋቶችን በንጽጽር ከህንጻዎቹ ጋር መመልከት ይኖርብናል።

በቦሌ መንገድ ላይ ርዋንዳ አካባቢ የነደፈው የናይል ሶርስ ህንጻ አንድ ምሳሌአችን ነው። በመደበኛ ሁኔታ የሚነደፉ መግቢያዎች ከህንጻው ጋር የሚመጣጠን ምጣኔ እና ሚዛናቸውን ጠብቀው ጎላ ስለሚሉ  አይናችንም ሆኑ አእምሮአችን በዚሁ መልኩ ያለ ሰው ወይም ተሽከርካሪ እርዳታ  የህንጻዎችን ሚዛን እና ምጣኔ ተረድቶ እና  ተርጉሞ ያልፋል።

ይህን መደበኛነት ከተጣሰ ግን አእምሮ ሚዛኑን እና ምጣኔውን ለመረዳት የግድ እነዚህን መለኪያ መስፈሪያዎች የሆኑትን ሰዎች እና ተሽከርካሪዎችን ማየት ይፈልጋል። ዘለቀ በናይል ሶርስ ህንጻ ላይ ያሉትን አያሌ የንድፍ ዝርዝሮችን ለመረዳት እንቆቅልሽ በሆነ መልኩ ከመደበኛው ልምምድ አስፈንግጦአቸዋል። 

መግቢያው፣ መስኮት ነክ ክፍተቶች፣ ሳጥኖች፣ ግዙፍ አርማታ ግንብ ወዘተ...ባልተለመዱ ምጣኔዎች የተነደፉ ናቸው።

እስቲ የናይል ሶርስ ህንጻን መግቢያ ከትክክለኛ የሰው  ምስሎች እና መጠናቸው  በአርትኦት ከተቀየሩ የሰው ምስሎች ጋር  እንመልከተው።

እርስዎ የትኛው ትክክል ምስል ነው ብለው ይገምታሉ? መልስዎትን በሚከተሉት ምስሎች ይግለጡ

ልብ ቅርጽ ❤️.....1ኛው ምስል
ጭብጨባ 👏... 2 ኛው ምስል
አውራጣት 👍....3ኛው ምስል

ጽሁፍ እና ምስል ከ ዳዊት በንቲ

@etconp
❤7👍1
September 13, 2026 1.4K 2